Download Awramba Times Issue 171 PDF

TitleAwramba Times Issue 171
File Size4.6 MB
Total Pages22
Document Text Contents
Page 1

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 171 ቅዳሜ ሰኔ 04 2003

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑበ ገፅ 11

በ ገፅ 19

4ኛ ዓመት ቁጥር 171 ቅዳሜ ሰኔ 04 2003 ዋጋ 7፡00 ብር

‹‹ወደዚህ የመጣሁበት ዋናው ምክንያትም ይኸው ነው። አዲስ አበባን ለመቆጣጠር

ስንዘጋጅ አሜሪካ ከጀርባችን መሆኗን ማረጋገጥ እንፈልጋለን። የእናንተ ድጋፍና

ምክር ለእያንዳንዱ እንቅስቃሴአችን ወሳኝ ነው። … ኢትዮጵያውያን ነጻነት

እና ዴሞክራሲ እንዲጎናጸፉ እንፈልጋለን። … ማርክሲስት - ሌኒኒስት

አይደለንም። ነገሮችን በአዎንታዊ መንገድ እንድትገነዘቡልን

እንፈልጋለን።››..... በዳዊት ከበደ....

የመለስና የ‹‹ሲ.አይ.ኤ››ው አባል ምስጢራዊ ውይይት

በ ገፅ 3

የመንግስት ተቋማትን
ገመና ያጋለጠው ሪፖርት

የዩ.ኤስ አሜሪካን የውጭ ጉዳይ
ሴክሬታሪ የሆኑት ሂላሪ ክሊንተን
በኢትዮጵያ የሁለት ቀናት
ዲፕሎማሲያዊ ጉብኝት ለማድረግ
የፊታችን ሰኞ አዲስ አበባ እንደሚገቡ
በኢትዮጵያ የሚገኘው የአሜሪካን
ኢምባሲ ለአውራምባ ታይምስ በላከው
መግለጫ እስታወቀ፡፡

ሂላሪ ክሊንተን በሁለት ቀን ቆይታቸው
በአፍሪካ ህብረት ዋና ጽህፈት ቤት

ተገኝተው ንግግር የሚያደርጉ ሲሆን፣
ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ጨምሮ
ከሌሎች የኢትዮጵያ መንግሥት
ባለሥልጣናትና የአፍሪካ ህብረት
ኃላፊዎች ጋር ይወያያሉ፡፡ በአሜሪካ
መንግሥት ድጋፍ የተቋቋሙ
ፕሮጀክቶችንም ይጎበኛሉ ተብሎ
ይጠበቃል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር የተሟላ ማስረጃ ሳይቀርብለት 1

ነጥብ 45 ቢሊዮን ብር ክፍያ ፈፅሟል

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ያለአግባብ

ከ10 ሚሊዮን ዶላር በላይ ለጀነሬተር ኪራይ ከፍሏል

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ በሕገ-ወጥ መንገድ ብዛቱ አምስት

ሺህ የሚሆን ጥራዝ የገንዘብ መቀበያ ደረሰኝ አሳትሞ

ሒሳብ ሰብስቧል

ኤች.አይ.ቪ/ኤድስን ለመከላከልና ለመቆጣጠር

የተመደበው ከፍተኛ ሀብት ለሌላ ዓላማ ውሏል።

የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የሕዝብ ተወካዮች ም/

ቤት ያጸደቀው በጀት የፋይናንስ አስተዳደር ሕጉን፣

ደንብና መመሪያ በሚፈቅደው መሠረት በትክክል

ሥራ ላይ መዋሉን ለማረጋገጥ በ2002 በጀት ዓመት

ሒሳብ ላይ ባከናወነው ኦዲት በርካታ የሒሳብ አያያዝ

ግድፈቶችን ማግኘቱንም አስታውቋል።

ሂላሪ ክሊንተን ሰኞ አዲስ አበባ ይገባሉ
በ ገፅ 21

በ ገፅ 19

የብርቱካን
የመኸር ጊዜእርሳቸው “በኢትዮጵያ ከታዩ ሥርዓቶች
ውስጥ ይህንን ሥርዓት በቀላሉ ማሸነፍ
ይቻላል” ብለው ያምናሉ። የኢህአዴግ ህልውና
የተመሰረተው በራሱ ጥንካሬ ላይ ሳይሆን
በተቃዋሚዎች ድክመት እና ሕብረት ማጣት
ላይ እንደሆነ ይገልፃሉ። አዎን፣ የዛሬ
ትንታኔያቸው ማጠንጠኛ ብርቱካን ናት።
ከፖለቲካው እርቃ ትቆያለች የሚል እምነት
የላቸውም። “በአሁን ሰዓት በኢትዮጵያ
አንዲት መልካም ፍሬ የምታፈራ የምታምር
ድንቅ ዛፍ ተተክላ በጥሩ ሁኔታ በቅላለች፤
ብዙ ውሽንፍርና ውርጭ ተቋቁማ ፍክት ብላ
አብባለች” በማለት ይተርኩና ሲደመድሙም፣
“እናም በፍሬው ለቀማ ላይ ወ/ሪት ብርቱኳን
ቅርጫቷን ይዛ ብቅ አትልም ብሎ መጠርጠር
የማይታሰብ ነው” ይሉናል።

አቶ አብርሃም ያየህ

የብተና ፖለቲካ
የወለደው አዲስ ምዕራፍ!

የብተና ፖለቲካ
የወለደው አዲስ ምዕራፍ!

ኢትዮጵያውያኑ
የተስፋ ፍሬዎች

በነፃ ገበያ ዙሪያ የሚነፍሰው
የተሳሳተ አመለካከት

በአለማየሁ ገ/ማርያም (ፕ/ር) በፈቃዱ በቀለ (ዶ/ር)

በ ገፅ 14 -15

ከሰሞኑ ‹‹የኢህአዴግ ደጋፊ አርቲስቶች ማኅበር›› ሳይቋቋም አይቀርም!

በ ገፅ 4

የአሲድ ጥቃት የተፈፀመባት አረፈች

‹‹የሠራዊት እና ሠራዊቱ ድራማ››
የኪነ-ጥበብ ‹‹ባለሙያዎች›› እና የጠቅላይ ሚኒስትሩ

ስብሰባ ቅሬታዎች በርክተውበታል

ለ20 ዓመታት ተፈትኖ የወደቀ አካል በቃህ ሊባል ይገባዋል!
መውጫው መንገድ ፀንቶ መታገል ብቻ ነው!

ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)

Page 2

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 171 ቅዳሜ ሰኔ 04 2003

T’@Í=”Ó ›?Ç=}`
Ç©ƒ ŸuÅ

ª“ ›²ÒÏ
õì<U TV

(›É^h ¾ካ ¡/Ÿ
kuK? 03/04 ¾u?.l 1540)

U/ª“ ›²ÒЋ
Ó³¨< KÑW
¨<wgƒ �Â

Ÿõ}— ›²ÒÏ
›u?M ¯KT¾G<

›²ÒÏ
¨c”cÑÉ Ñ/Ÿ=Ç”


Ÿõ}— ]þ`}a‹

›?MÁe Ñw\
c<^õ›?M Ó`T

ኮፒ ኤዲተር
ƒ°Óeƒ ¨”ÉS<

¯UÅ™‹
cKV” VÑe

ታዲዎስ ጌታሁን
SpÅe õeN
ደሳለኝ ስዩም

iÁß“ Te�¨mÁ
}hK cÃñ
0911629281


Ó^ò¡e ›?Ç=}`
’w¿ Seõ”

(0911 18 09 33)
E-Mail:[email protected]

የማስታወቂያ ክፍሉ ስልክ
0911629281

¾´Óσ ¡õK< eM¡
eM¡:- ®911 62 92 78
®911 62 92 82
0911 15 62 48

þ.X.l 7994
[email protected]
http://www.awramba.com

›d�T>¨<
ብሉ ኤርዝ ጀነራል ቢዝነስ

ኃላ/የተ/የግል/ማህበር

ር ዕ ሰ አ ንቀፅ

ማን ምን አ ለ

2


ድንገት ተቀጣጥሎ
የአረብ አገራትን ማዳረስ
የጀመረው ሕዝባዊ
አብዮት ለ42 ዓመታት
ያህል የአፍሪካዊቷ ሊቢያ

አድራጊ ፈጣሪ በነበሩት ኮሎኔል
ሙአመር ጋዳፊ ላይም ሲቀጣጠል
ሰውየው በተቃወሟቸው ዜጎቻቸው
ላይ የግድያ ብይን በይነው ዕልቂት
አወጁ፡፡ ይህን ተከትሎም ዩናይትድ
ስቴትስ አሜሪካን፣ ፈረንሳይ እና
እንግሊዝ በጋዳፊና ደጋፊዎቻቸው
ላይ የአፀፋ ምላሽ ለመስጠት
የሚያስችል ወታደራዊ ድጋፍ
ለተነሱባቸው የሀገሪቱ ኃይሎች
በማቅረብ የተጠበቀውን ፍልሚያ
ጀመሩ።

ምንም እንኳ በጋዳፊ
ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት የበገነው የዓለም
ሕዝብ ለጥምር ኃይሉ ያለውን
ድጋፍ ቢገልጽም፣ አሜሪካውያን
ግን ከራሳቸው ብሔራዊ ፍላጎትና
ጥቅም ጋር የተያያዘ አንድ መጠይቅ
ወዲያውኑ አቀረቡ፡፡

የሕዝቡን ፍላጎት
በሚያንሸራሽሩ የአገሪቱ መገናኛ
ብዙኃን አማካይነት የቀረበው ጥያቄ፣
‹‹በዚህ ከፍተኛ ወጪ በሚጠይቅ
ወታደራዊ ግዳጅ የአሜሪካ ፍላጎትና
ጥቅም ምንድነው?›› የሚል ነበር፡
፡ የተለዩ አመክንዮዓዊ መሰረቶችን
በመዘርዘር የሚነቅፍ ነው የጥያቄው
አንደምታ። እናም ሳይውል ሳያድር
የፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ምላሽ
ተሰማ።

በመገናኛ ብዙኃንም
ቀርበው፣ ‹‹አዎ፤ በዘመቻው
ተሳትፈናል። ይህን ያደረግነውም
አምባገነኖች ሕዝባቸውን ሲጨፈጭፉ
የሞራል እና ዓለም አቀፍ ሰላም
የማስጠበቅ ግዴታ ስላለብን ነው›
ሲሉ ገለፁ፡፡

ሌላው የማይዘለል ነጥብ
ደግሞ ፍጹም ዴሞክራሲያዊነት
በተንፀባረቀበት ሁኔታ በዘመቻው
ላይ ከራሳቸው የዴሞክራቲክ
ፓርቲ አባላት ሳይቀር ተቃውሞ

የገጠማቸውን ያህል፣ የፓርቲያቸው
ተቀናቃኝ ከሆነው ሪፑብሊካን ፓርቲ
ድጋፍ የቸሯቸውም ነበሩ፡፡

ጥያቄው፣ ይህ ተሞክሮ
ለአገራችን መሪዎች ምን ያስተምራል
የሚል ነው። ከዚህ ጋር አያይዘን
የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት
ባለሥልጣናት እና በሚዲያዎቻቸው
ሲገለፅ የነበረን ስናስታውስ ልዩነቱንና
ለልዩነቱ ምክንያት የሆኑትን
ጉዳዮች በግልፅ ያመላክተናል ብለን
እናምናለን።

እንደሚታወሰው ሁሉ
የኢትዮጵያ ጦር ወደ ሶማሊያ
ዘምቷል በሚል አል-ጃዚራ የተሰኘው
ዓለም አቀፍ የቴሌቪዥን ጣቢያ እና
ሌሎች ሚዲያዎች ምስል እያስደገፉ
ጉዳዩን ለዓለም ሕዝብ አቀረቡ።
የኢህአዴግ መንግሥት ምላሽ ግን
ሁነቱን ሙሉ ለሙሉ ያስተባበለ
ሆኖ ተከሰተ። ዘግይቶ ግን የአል-
ሻባብ መሪ በኢትዮጵያ ላይ ‹‹ጅሃድ
አውጀናል›› በማለቱ ቀደም ሲል
የነበረው ማስተባበያ ተቀየረ። ይህንኑ
ተከትሎ በየደረጃው ያሉ ሹማምንት
አቋማቸውን ቀይረው አዲሱን
መግለጫ ማቀንቀን ጀመሩ።

‹‹አድርገናል፤ ያደርግነውም
ለዚህ ዓላማ ሲባል ነው›› በሚል
ለሕዝብ በታማኝነትና በግልፅ
የመንገር አሰራር የሌለ ከመሆኑም
በተጨማሪ፣ ሁኔታውን ሚዛናዊ
ለማድረግ እንዳያስችል እንኳ
በሥርዓቱ ውስጥ ከላይ እስከታች
የሚገኙ ሹማምንት በምንም መልኩ
ይገለፅ ከማስተጋባት ውጪ በዚህ
ላይ የተለየ ኃሳብ አለኝ በሚል
የአማራጭ አቅጣጫ ሲያመላክቱ
አናይም። ይህም ለማንኛውም ዜጋ
አሳሳቢ አካሄድ ነው፡፡

ይህ ሁኔታ ‹‹ከእኛ ጋር
ያልሆኑ ሁሉ ከእኛ በተቃራኒ
የቆሙ ናቸው›› ከማለት አልፎ፣
የተለየ አስተሳሰብ ያላቸውን
ወገኖች በሚያነሱት ኃሳብ
ወይም በሚያራምዱት የፖለቲካ
ርዕዮት-ዓለም ምንነት ሳይሆን

በመሰረተ ልዩነቱ ብቻ ሲታገሉት
ይስተዋላል።

ቆጥረን የማንጨርሳቸው
ሆኖም አካሄዳቸው በትውልዱ
አስተሳሰብ እጅግ አደገኛ ጫና
የሚያሳርፉ ክንውኖችን መሪዎች
ሲገልፁ፣ በየደረጃው ያሉ አመራሮች
ሲያራግቡ፣ ከላይ ያለው አመራር
አቋሙን ሲቀይር ወዲያው ብዙ
የተባለለትን ሁነት አፈር አልብሶ
አዲሱን መዝሙር መዘመር
ለገዢው መንግስት ጠቅሞታል
የሚል መከራከሪያ ቢቀርብ እንኳ
ሕዝቡን ውዥንብር ውስጥ እየከተተ
መቀጠሉ አጠያያቂ አይደለም።
በተለይ አንዳንዶቹ ጉዳዮች መዘዛቸው
በቀላሉ የማይመዘዝ መሆኑን
ማስተዋል ይገባል። የመሪዎች ኃሳብ
መዋዠቅ ምናልባት ድርጅታዊ
ጠቀሜታን ‹‹ያስገኛል›› ተብሎ
ታምኖበት ተወስዶ ሊሆን ይችላል፡፡
እኛ ግን ያ የሚያስከትለው አገራዊ
ምስቅልቅል እጅግ እጅግ ያሳስበናል!

ከዓመታት በፊት
ማቆጥቆጥ የጀመረውን የኑሮ
ውድነት እና የዋጋ ግሽበት
ለመከላከል መደረግ ስለሚኖርበት
የቁጥጥር ሥርዓት ከአንዳንድ የነፃ
ፕሬሶች፣ ከምሁራኑ እና ከሕዝቡ
ይቀርቡ ለነበሩ አማራጮች ጠቅላይ
ሚኒስትር መለስ፣ ‹‹የሚመራን
ገበያው ነው፤ የምንከተለው የኢኮኖሚ
ፖሊሲም ይህንኑ መሰረት ያደረገ
ነው›› ሲሉ የሰጡት ምላሽ አሁን
ድረስ በጆሮአችን የሚያቃጭል
ነው፡፡ በኋላም በየደረጃው ያሉ
የመንግሥታቸው ባለሥልጣናት
ይህንኑ በጠነከረ አፅንኦት ሲገልፁ
ተደመጡ፡፡

አይደለም የተለየ ኃሳብ
ያቀረበ፣ ከዚህ የተለየ ኃሳብ ሲነሳ
የነበረው ምላሽ በጠንካራ ተቃውሞ
የታቃኘ ነበር። ቆይቶ ግን፣ ማለትም
ከአምስት ወራት በፊት፣ በመሰረታዊ
ሸቀጦች ላይ በተደረገ የዋጋ ትመና
ለዓመታት የተቀነቀነው ወደ ጎን
ተደረገ።

ያንንም ተከትሎ ላለፉት
አምስት ወራት ከላይ እስከታች
የነበሩ የገዢው መንግሥት
ሹማምንት ስለዋጋ ተመኑ
በማይታጠፍ አቋም ሲከራከሩ ቆዩ።
አሁንም ከላይ ያለው አቋሙን ቀየረ፡
፡ እናም ከአምስት ወራት በኋላ ወደ
‹‹ገበያው ይመራናል›› ተመለስን።
እንዴት? በምን አግባብ? ቀጣዩስ
ጉዞ? በሚለው ላይ የተለያዩ ኃሳቦች
ሲንሸራሸሩ ግን እያየን አይደለም።
አይተመን? አዎ! ይተመን? አዎ!
ወደ በፊቱ እንመለስ? አዎ፡፡ አዎ፣
አዎ፣ አዎ ተብሎ የት ይደረሳል?
...

‹‹ኢትዮጵያ ሬዲዮኖችን
ታፍናለች› የሚል ክስ ይቀርብባት
የጀመረው በቅርብ ጊዜያት አይደለም።
ከላይ ያሉት ‹‹ሐሰት ነው›› አሉ።
በየደረጃው የሚገኙት ‹‹በሬ ወለደ
ነው›› ሲሉ ቆዩ። ጠቅላይ ሚኒስትር
መለስ ግን ‹‹አቅሙ እስካለን ድረስ
እናደርገዋለን፤ እንዲያውም ትዕዛዝ
ሰጥቻለሁ›› ሲሉ ደግሞ የዓለም አቀፍ
ተሞክሮዎችን ሳይቀር እያጣቀሱ
ሚዲያዎችን መሸበብ የተለመደና
የሚገባ መሆኑ ተዘከረልን። ሁላችንም
እንደምናውቀው ዛሬ አገራችን ሬዲዮ
ጣቢያዎችን ብቻ ሳይሆን፣ ከሰሐራ
በታች ድረ-ገጾችን በማፈን ከአናቶች
አናት ላይ ተቀምጣለች።

ቀደም ሲል እንደጠቀስነው፣
ስፍር ቁጥር የሌላቸው መሰል
ተሞክሮዎችን መደርደር እንችላለን።
ዋናው መልዕክታችን የተባለውን
ሁሉ እንደወረደ የሚያስተጋቡ
የመንግሥት ባለሥልጣናት
‹‹ሕዝባቸውን›› በሁለንተናዊ
መንገድ እጅግ አስከፊ በሆነ
መልኩ መጉዳታቸው አይቀርምና
ከተግባራቸው ለመታቀብ ቆም
ብለው ያስቡ ነው፡፡ ለሕሊናቸውም፣
ለሕዝቡም ታማኝ ሊሆኑ ይገባቸዋል
ብሎ ማሳሰብ ነው።

ኢትዮጵያ ለዘላለም
ትኑር!!!የካቲት 2000 ዓ.ም ተመሠረተ

አውራምባ ታይምስ፡- በብሉ
ኤርዝ ጀነራል ቢዝነስ ኃላ/የተ/
የግል/ማህበር ስር የሚታተም፤
በፖለቲካዊና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ
የሚያተኩር፤ በንግድ ሚኒስቴር
በቁጥር 020/2/6572/2001
የተመዘገበ ሳምንታዊ ጋዜጣ ነው፡፡

አድራሻ
አራዳ ክ/ከተማ ቀበሌ 09

የቤት ቁጥር 191

ከአራት ኪሎ ወደ ፒያሳ በሚወስደው
መንገድ ፣ ከራስ መኮንን ድልድይ አለፍ
ብሎ ወደ ሀገር ፍቅር ቲያትር መገንጠያ
አስፋልት ላይ በሚገኘው ባህረ ነጋሽ
ሕንፃ ግቢ ውስጥ፡፡

አታሚ፡-

ብርሃንና ሰላም
ማተሚያ ድርጅት
ክ/ከተማ፡- አራዳ
ቀበሌ፡- 17
የቤት ቁጥር፡- 984

‹‹ለእኔ ምንም አይነት ትርጉም የለውም…
ምክንያቱም ጥቂት ሰዎችን በማሰርና
በመፍታት አገራዊ መግባባት መፍጠር

አይቻልም… በእነዚሁ ሰዎች የፍርድ ሂደት
ውስጥ የህዝብ ተሳትፎ የለም። ህዝቡ ይቅር

አልተባባለም››
ዶ/ር ያዕቆብ ኃ/ማርያም

የቀድሞው የተባበሩት መንግስታት ከፍተኛ
አቃቤ ህግ

‹‹አሁን በኢትዮጵያ ካለው ተጨባጭ ሁኔታ
አንፃር የእነዚህ ሰዎች መፈታት ያለው

ተፅዕኖ ምን ይመስላል?›› በሚል የደርግ
ባለሥልጣናትን በማስመልከት ከሰንደቅ ጋዜጣ

ለቀረበላቸው ጥያቄ የሰጡት ምላሽ።

‹‹ ‘ራቁቱን የተወለደ ዳባ መች አነሰው’
ይባላል። ባያተርፍም ከደጅ ጥናትና ከጉቦ

ተላቀን መኪኖቻችንን በአግባቡ መስራታቸው
በራሱ ለእኛ ሀብት ነው።››

አቶ ፀጋ አስማረ
የተባበሩት የነዳጅ ኩባንያ የቦርድ ሊ/መንበር
‹‹የነዳጅ ስራ በኢትዮጵያ አትራፊ አይደለም

እየተባለ ይነገራል። እውነት አትራፊ
አይደለም?›› በሚል ከሪፖርተር ጋዜጣ

ለቀረበላቸው ጥያቄ የሰጡት ምላሽ።

የመሪዎች ሀሳብ መዋዠቅ የሚያስከትለው
አገራዊ ምስቅልቅል እጅግ እጅግ ያሳስበናል

ማን ምን አ ለ

‹‹ጥሩ አይደለም! ይሄ ግልጽ ነው። ተወልጄ
ያደግኩባትን እናት አገሬን አጥቻለሁ።

ከወገኔ ተለይቻለሁ።››

ሌተናል ኮሎኔል መንግስቱ ኃ/ማርያም
የቀድሞ የኢህድሪ ፕሬዚዳንት

ግንቦት 13 ቀን ከኢትዮጵያ የለቀቁበትን 20ኛ ዓመት
አስመልክቶ ከጋዜጠኛ ደረጀ ኃይሌ ጋር በኢትዮፒካ

ሊንክ የሬዲዮ ፕሮግራም ባደረጉት ቃለ-ምልልስ
ሥለስደት ከተናገሩት።

Page 11

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 171 ቅዳሜ ሰኔ 04 2003

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

11

p Ç [email protected] S ´ “ —

ጳውሎስ ኞኞ ይሰራበት በነበረው አዲስ ዘመን
ጋዜጣ የ‹‹አንድ ጥያቄ አለኝ›› አምድ
የካቲት 1964 ዓ.ም. እትም ላይ ‹‹እስካሁን
ድረስ በኢትዮጵያ በብዛት የሌለው ስም የቱ
ነው?›› የሚል ጥያቄ ቀርቦለት፣ ‹‹ኞኞ
ነው›› ሲል መልሷል። የተጠየቅከው አንተ
ብትሆን ደግሞ ‹‹ማንዶዬ›› የምትል
ይመስለኛል።
አዎ፣ ማንዶዬ የተለመደ ስም አይደለም።
አባቴ የደቡብ ሰው ነው፤ የወላይታ።
የስሙ አቻ የአማርኛ ቃል ‹‹ማንን
ተክቼ›› እንደ ማለት ነው።

አንተን የሚያስታውስ ‹‹እሁድ የእቁብ
ጠላ›› የሚለውን ኮሜዲያዊ የሙዚቃ ስራን
አይዘነጋም።
የዘፈኑ የዜማና የግጥም ደራሲ ንጉሱ
ረታ ይባላል። በወቅቱ ጠጪ ስለነበርኩ፣
ይመለከተኝ ስለነበር ለእኔ ሲሰጠኝ ደስ
ብሎኝ ተጫወትኩት።

በርካታ ጣሳ ጠላ ትጠጣ እንደነበር ሰምቻለሁ።
ምን ያህል ትጠጣ ነበር?
ኦው! ጠዋት ተነስቼ ጠላ ነበር
የምጠጣው። [ይጠጣ የነበረው ዶሮ
ማነቂያ ውስጥ በሚገኘው ሾፌር ሰፈር
ነበር።]

ጠዋት ከ40 በላይ ብርጭቆ ትጠጣ ነበር አሉ

ያኔ በብርጭቆ አይለካም እንጂ ከዚያ
በላይ ጠጣ ነበር። ጠላ የምንጠጣው
ጠዋት ጠዋት ብቻ ነበር። ከዚያ በኋላ
ወደ ካቲካላ፤ ጠጅ እንቀጥላለን። እስከ
ምሽት ድረስ መጠጣት ነበር። [በወቅቱ
የሁለት ጣሳ ጠላ ዋጋ ስሙኒ ነበር።]

ከ60 ዓመት የሕይወት ተሞክሮህ አንፃር
ስታየው፣ ‹‹ባልፈጠር ያመልጠኝ ነበር››
የምትለው ነገር ምንድን ነው?
መጠጥ ካቆምኩ 24 ዓመት ደፍኖኛል።
በፊት ብሞት መጠጥ ገደለው እንጂ
እግዚአብሔር ገደለው አይባልም ነበር።
ኖሬ ይህን በማየቴ ደስ ይለኛል። በመኖሬ
ብዙ የሰው ፍቅር አግኝቻለሁ። ባልፈጠር
ይህ የሕዝብ ፍቅር ከየት ይገኝ ነበር?

ከሰውነትህ አካላት መካከል ቢቀነስም
አይጎዳኝ የምትለው አለ?
ሁሉም የሰውነት አካላት ጠቃሚ ናቸው።
ኧረ! ይቀነስ የምለው የለም።

የፊት ገፅታህ ቁጡ ያስመስልሀል። ዝምታህም
የሚያስጨንቅ አይነት ነው ልበል?
ብዙዎች እንደዚያ ይሉኛል። ከመናገር
ይበልጥ ማዳመጥ ደስ ይለኛል። ብዙ

ክርክር አልችልም። የማውቀውን ነገር
እንኳን ‹‹አይደለም›› ቢሉኝ ከምከራከር
ይልቅ አምኜ ብለያይ ብዬ ስለማምን
እተወዋለሁ። ዝም እና ኮስተር በማለቴ
ብዙ ሰዎች የምጫወት አይመስላቸውም።
ድሮ ድሮ ጠጅ ቤት ውስጥ ዝም ስለምል
ተደባዳቢ መስላቸው ነበር። አንድ ሽማግሌ
ከቀረቡኝ በኋላ፣ ‹‹ለፀብ የተዘጋጀህ
እንጂ ተጨዋች ሰው አትመስለኝም››
ሲሉ ተዋውቄያቸው ለብዙ ዘመን ጓደኛ
ሆነናል።

የ‹‹እኔ›› የምትለው መልካም ነገር ምንድን
ነው?
በጎ ነገሮችን ለመስራት እሞክራለሁ።
በጓደኞቼ ላይ አንዳንድ ችግሮች ሲመጡ
በአቅሜ መተባበር እፈልጋለሁ። ሜሪ ጆይ
የተራድኦ ድርጅት ውስጥ የበጎ ፈቃድ
አገልግሎት እሰጣለሁ። የቀይ መስቀል
አባል ነኝ። ይህን መሰል በሆኑ በጎ
ሥራዎች ላይ ብካፈል ደስተኛ ነኝ።

የመኖሪያ አካባቢ በድርቅና በመሰል ችግሮች
ሳቢያ ‹‹ለኑሮ አመቺ አይደለም›› ሲባል
ሰፈራ ይደረጋል። የሙያ ሰፈራ ቢኖር ወደ ምን
መስፈር ትፈልጋለህ?
ወደ ሌላ ሙያ ብዘዋወር መስራት የምችል
አይመስለኝም። እንደገና ልጅ ብሆን ግን
እግር ኳስ ተጨዋች ብሆን ደስ ይለኛል።

ከሰራኸው ቲያትር ውስጥ እንደው ቢቻልና
በተመሳሳይ ሰዓት ‹‹ተዋናይ ሆኜ ብትሰራው፣
ተመልካች ሆኜ ባየው›› ብሎ ያስመኘህ አለ?
በ1964 ዓ.ም ‹‹ጤና ያጣ ፍቅር›› የሚል
ሙዚቃዊ ድራማ ሰርተን ሲጠናቀቅ
የነበረው ጭብጨባ በጣም ከፍተኛ ነበር።
ተመልካችም ሆኜ የማየው ቢሆን እሱን
መርጥ ነበር። ሌላው ቀርቶ በፊልም
ተቀርጾ እንኳን ባየው ደስ ይለኝ ነበር፤
ግን አልተደረገም።

ምላሽ ባለማግኘትህ ብቻ አምነህ የተቀበልከው
ነገር አለ?
አለ። እሱም በመስሪያ ቤታችን (በአዲስ
አበባ ቲያትርና ባህል አዳራሽ) ያለውን
የሠራተኛ ደረጃ አመዳደብ ነው። አንድ
ጊዜ ኤክስፐርት ያደርጉሀል፣ ሲፈልጉ
ተዋናይ ያደርጉሀል። እናም ሳላምንባቸው
ብዙዎቹን ነገሮች ተቀብያለሁ። ‹‹ለምን?››
ብትለኝ እነሱ ማሟላት አለብህ የሚሉኝን
የትምህርት ሰርተፍኬት ስለማላሟላ ነው።
እኔ ትምህርት ያቆምኩት 7ኛ እና 8ኛ
ክፍል ላይ ስለሆነ ያሉኝን መቀበል ነው።
በችሎታ /በሙያ ፈትነው ኤክስፐርት፣
ተዋናይ ስድስት ተብዬ ነበር። እንደገና
በቢ.ፒ.አር ተራ ተዋናይ ተብዬ ወደ

ታች ስወርድ በዚህ ምክንያት ጡረታ
ወጥቻለሁ። [ጡረታ 1,067 ብር ያገኛል]

ባለፈው ሰኞ የጥበብ ‹‹ባለሙያዎች››
ከጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ጋር ባደረጋችሁት
ስብሰባ ላይ አንተ የተሳተፍክበት ተውኔት
አቅርባችኋል። ‹‹ልቤን የጭብጨባ ቡፌ
አጥግቦት ሆዴ ባዶ መሆኑን እያወቅኩ
ይኸው እስከዛሬ ዘለቅኩ›› የሚል የጥበብ
ሰዎች ኑሯችሁ አሳዛኝ መሆኑን የሚገልፅ ቃለ
ተውኔት ከአፍህ ወጥቷል። ይህ መሰል ነገር
ተደጋግሞ ይነሳል። እናንተ የሙያው ፀባይ
ታዋቂ ያደርጋችኋል፣ ጭብጨባ ይቸራችኋል።
አንድ የሕክምና ዶክተር፣ አካውንታንት፣ ሥራ
አስኪያጅ አይጨበጨብላቸውም እንጂ ትልቅ
ነገር ይከውናሉ። የእናንተ ታዲያ ምን ስለሆነ
ነው ተደጋግሞ የሚነሳው?

የቴሌቪዥን ድራማ፣ ፊልም እና ሌሎች
የጥበብ ውጤቶችን ስንሰራ የሚከፈለን
ገንዘብ አነስተኛ ነው። ይህ እንዲሆን
ያደረገው ደግሞ የቅጂ መብት በአግባቡ
አለመከበር ነው። በእኛ ሥራ ምንም
ነገር ሳይሰሩ ትልቅ ሀብታም የሆኑ
ሰዎች አሉ። አሁን በህይወት የሌለ
አረብ አገር ይኖር የነበረ አንድ ጓደኛችን፣
‹‹የሚገርማችሁ የእናንተ ድራማ
ሲተላለፍ እዚያ እሸጥ ነበር። ገንዘቡ
የቤት ኪራይ ለመክፈል ይረዳኝ ነበር››
ብሎኛል። እሱ ግልፅ ስለሆነ ነገረን እንጂ
ብዙዎች ተጠቃሚ የሆኑ አሉ። ይህ
ደግሞ ተገቢውን ህይወት እንዳንመራ
አድርጎናል እንጂ፣ ‹‹እኛ ከሌላው ህዝብ
የተለየን ነን›› ማለት አይደለም።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን
ፓትርያርክ ሙሉ መጠሪያ ስማቸውን
ታውቀዋለህ?
[እየሳቀ] አታስቸግረኝ … በእውነት
ጥራ ብትለኝ አልችለውም። [እንደምንም
ሞክረው ብዬው ዝግ እያለ ቀጠለ] ብፁዕ
አቡነ ጳውሎስ ፓትሪያርክ አክሱም
ወይጨጌ እንደዚህ የሚል አለበት እና
አዎ እንደዚያ ነው …·ረ ይጠፋኛል።
[ለማንኛውም ፋንቱ እኔ ልሞክር…
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት
ዘኢትዮጵያ፣ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም፣
ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፣
የዓለም አቢያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት
ፕሬዝዳንት፣ የዓለም ሃይማኖቶች ምክር
ቤት ለሰላም የክብር ፕሬዝዳንት፣… ኦው!
ፋንቱ የቀረ ካለ ተባበረኝ፤ እንሞላዋለን፣
ስለ ትብብርህ አመሰግናለሁ።]

ለ42 ዓመታት በኪነ-ጥበብ ውስጥ ቆይታ ያደረገ

አንጋፋ የጥበብ ሰው ነው። ‹‹እሁድ የእቁብ ጠላ›› እና

ከፀሐይነሽ በቀለ ጋር የተጫወተው ‹‹የት ሄደሽ ነበር … ››

የሚሰኙት ኮሜዲያዊ ዜማዎች (ሙዚቃዊ ድራማዎች) አይረሴ

አድርገውታል። 40 ገደማ የሚሆኑ የመድረክ ቲያትሮች ላይ

ተሳትፏል። ‹‹የቅጂ መብት አለመከበር ተገቢውን ጥቅም

እንዳናገኝ አድርጎናል›› የሚለው ፋንቱ ማንዶዬ፣ አንዳፍታ
የአቤል ዓለማየሁን ጥያቄዎች ይመልሳል።

አ ፍታ1
‹‹በቢ.ፒ.አር ተራ ተዋናይ ተብዬ

ወደ ታች በመውረዴ ጡረታ ወጥቻለሁ››
ፋንቱ ማንዶዬ [አርቲስት]

“ኦዉሽ” ነጠላ ግጥም ተለቀቀ
የአረንቻታ ማስታወቂያ ባለቤትና የአርከባስ መፅሔት ዋና አዘጋጅ

የሆነው ጀሚል ሰኢድ በብዕር ስሙ ኪፍያፍ (ሃጅ) “ኦውሽ” የተሰኘ ለአባይ
ዶክመንተሪ ቅኔ ሲዲ አሣተመ። ግጥሙን ታዋቂ ምሁራን ገምግመውታል።
ማጀቢያ ሙዚቃውን ድምፃዊ ማሚላ (አውአውባዴ)፣ ቅንብሩን ካሙዙ ካሣ
ሰርተውታል። ሲዲው በነፃ የሚሠራጭ እንደሆነና ሙሉ ወጪው ሃያ ሺህ ብር
መሆኑን የገለፀው ጀሚል (ኪፍያፍ) በቀጣይነት ክሊፕ ተሰርቶለት በመላው
አለም እንደሚሰራጭ፤ በቀጣይም ሙሉ ስራውን ለህዝብ እንደሚያቀርብ እና
ለህትመት የተዘጋጁ መፅሐፎቹን እንደሚያሳትም ገልጿል።

“ዘኪዮስ” እና “ፔሌማ” ፊልሞች ይመረቃሉ
በሱራፌል ተምትም ተደርሶ በሄሮን ስቱዲዮ የቀረበው “ዘኪዮስ”

የተሰኘ ፊልም ነገ በ8፡00 ሰዓት በአለም ሲኒማ በልዩ ሁኔታ እንዲሁም በመላው
ኢትዮጵያ ይመረቃል። የፊልሙ ጭብጥ አንድ በቁመቱ ድንክ የሚባል
ሰው ለህይወት ስኬት ሲታትር የሚያሳይ ሲሆን በርካታ የማህበራዊ ጉዳዮችን
ይዳስሳል።

ሸዋፈራሁ ደሳለኝ፣ ፍቅርተ ጌታሁን፣ ሞዴል ሰብለ ወንጌል ፀጋ፣
አለምሰገድ ተስፋዬ ገነነ አማረ እና ሌሎችም ከ120 በላይ አርቲስቶች የተካፈሉበት
ይህ ፊልም ከ600 ሺህ ብር በላይ ወጪ እንደወጣበት አዘጋጆቹ ገልፀዋል።

እንዲሁም በባሮክ ፊልም ፕሮዳክሽን የቀረበው የደራሲና ዳይሬክተር
ሜሊ ተስፋዬ “ፔሌማ” ልብ አንጠልጣይ ፊልም የፊታችን ሰኞ ከምሽቱ 11፡00
ሰዓት በብሔራዊ ቴአትር፣ በአለም ሲኒማ በዮፍታሔ ሲኒማ፣ በሴባስቶፖል እና
በሌሎችም ሲኒማ ቤቶች ይመረቃል።

ፊልሙ “አዋቂ ጠንቋይ” ጋ የሚሄዱ ሦስት ጓደኛሞች ህይወት ዙሪያ
የሚያጠነጥን ሲሆን መልካም የመሰለ ክፉ ነገር ሁሉ መጨረሻው ውድ ዋጋ
የሚያስከፍል ስለመሆኑ የሚያስቃኝ መሆኑን ፕሮዳክሽኑ ገልጿል።

በፊልሙ ላይ ማክዳ ሃይሌ፣ ማስረሻ ደጌ፣ ሄለን ቸርነት፣ ናትናኤል
ጌታቸው እና ሌሎችም ተውነውበታል።

‹የአቤ ቶኪቻው ስላቆች› በመጽሐፍ መልክ ቀረበ
አቤ ቶኪቻው የተሰኘ የብዕር ሥም በመጠቀም በአገሪቷ ፖለቲካዊ

ማሕበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ዙሪያ በአውራምባ ታይምስ ጋዜጣ ላይ በመጻፍ
የሚታወቀው አበበ ቶላ በተለያየ ጊዜ ያቀረባቸውን 27 ስላቃዊ መጣጥፎች
በመፅሐፍ መልክ ታትመው ለአንባብያን ቀረቡ።

ከእነዚህ 27 ሰላቃዊ መጣጥፎች መሀል አብዛኞቹ በሳምንታዊዋ
አውራምባ ታይምስ ጋዜጣ ላይ ለንባብ የቀረቡ መሆናቸውን ፀሐፊው ገልጿል።
አበበ ቶላ ‹‹ስላቆች ከአቤ ቶኪቻው›› በሚል ርዕስ ለአንባቢያን ያቀረበው
ይህ መፅሐፍ ባለ 152 ገፅ ሲሆን በ26 ብር ዋጋ እየተሸጠ መሆኑን ለማወቅ
ተችሏል።

የብልጽግና ቁልፍ ቁጥር 4 ታተመ
በምንኖርበት የውድደር ዓለም ላይ ዕድገትን በመሻት ተግተው

ለሚሰሩ፣ የተሻሉ የዕድገት ስልቶችን በአማራጭነት የያዘ ነው የተባለለት
‹‹የብልፅግና ቁልፍ ቁጥር 4›› መፅሐፍ ለህትመት በቃ።

የመፅሐፉ አዘጋጆች በኢተርፕሬነርሽፕ አሰልጣኝነታቸው የሚታወቁት
ዶ/ር ወሮታው በዛብህና የአዲስ አድማስ ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል ባልደረባ የሆነው
ጋዜጠኛ ብርሃኑ ሰሙ ናቸው።

‹‹የብልፅግና ቁልፍ ቁጥር 4›› መፅሐፍ ባለ 149 ገፅ ሲሆን፣ ለገበያ
የቀረበው በ29 ብር ከ99 ሳንቲም ነው።

“የንፁሐን ሰቆቃ በጓንታናሞ” እና “ሰውየው ማነው” መፅሐፎች ለገበያ
ቀረቡ

የታሪኩ ባለቤት ሙራት ኩርናዝ ከሔልመት ኩን ጋር በመተባበር
“የንፁሐን ሰቆቃ በጓንታናሞ” የሚል ርዕስ ያለውና ንፁህ ሰው ለአምስት ዓመታት
በጓንታናሞ እስር ቤት ያሳለፈውን ስቃይ በዝርዝር የሚተርክበት እውነተኛ ታሪክ
መፅሐፍ በቢኒያም አለማየሁ ተተርጉሞ ለገበያ ቀረበ። መፅሐፉም 239 ገፆች
አሉት።

በተያያዘ ዜና በቺካጎ አሊኖስ ዲፖል ዩኒቨርስቲ የታሪክ ፕሮፌሰር
በሆኑት ዶ/ር ቶማስ ሞካይቲስ የተፃፈው ‹‹Osama Bin Laden biography››
በመሐመድ ኢብራሂም ሲራጅ አመካኝነት ‹‹ሰውየው ማነው›› በሚል ርዕስ ወደ
አማርኛ ተተርጉሞ ለህትመት በቅቷል።

ለበርካታ ዓመታት የዓለም ህዝብ የመነጋገሪያ ርዕሥ የነበረውና
በቅርቡ በአሜሪካዊያን ኮማንዶዎች ፓኪስታን ውስጥ የተገደለውን የኦማሳ
ቢንላደንን የህይወትና የህልፈት ታሪክ ያካተተው ‹‹ሰውየው ማነው?›› መፅሐፍ
230 ገጾች ያሉት ሲሆን ለአንባቢያን የቀረበው በ35 ብር ዋጋ እንደሆነም
ለማወቅ ተችሏል።

Page 12

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 171 ቅዳሜ ሰኔ 04 2003

የብርቱካን የመኸር ጊዜ

የቢስ አትክልትና
ፍራፍሬ አክሲዮኖች

በፍጥነት በመሸጥ ላይ
ናቸው።

እርሶም ፈጥነው
የዚህ ግዙፍና ትርፋማ

አክሲዮን ባለቤት
ይሁኑ!!!

12 እ ን ግ ዳ


ቅ ን ጅ ት
መሰባበር
በ ኋ ላ
ሁ ለ ት
ኃ ይ ሎ ች
ጎ ል ተ ው

ወጥተዋል። አንዱ በሰላማዊ ትግል
እቀጥላለሁ ያለው፣ በወ/ት ብርቱካን
የሚመራው የአንድነት ፓርቲ ሲሆን
ሌላው ደግሞ በሰላማዊ መንገድ
መታገል ያበቃለት ስለሆነ ሁሉንም
አማራጮች መጠቀም ግድ ይላል
የሚል አቋም የያዘው፣ በዶ/ር
ብርሃኑ ነጋ የሚመራው የግንቦት-7
ንቅናቄ ነው። እነዚህ ሁለት የተለያዩ
የትግል ስልቶች የያዙ ኃይሎች
አንዳንድ የሚመሳሰሉባቸው የጀርባ
ታሪክም አላቸው። የሁለቱም
ኃይሎች መሪዎች ታዋቂ የቅንጅት
አመራር አባላት የነበሩና ለቅንጅቱ
መፈጠር ወሳኝ አስተዋጽኦ የነበረው
የቀስተደመና ፓርቲ አመራር አባላት
የነበሩ ናቸው። ሁለቱም ኃይሎች
በአገር ቤትም ይሁን ከአገር ውጭ
ባለው የቅንጅት ደጋፊ ሕዝብ፣
በተለይም በወጣቱ ትውልድ፣ ጠቀም

ያለ ተቀባይነት ያላቸው ኃይሎች
ናቸው።

ሌላው የሚያመሳስላቸው
ነገር ደግሞ ሁለቱም ኃይሎች

ነገ ሰኔ 5 ቀን
ከሰኞ ጀምሮ በሁሉም ሲኒማ ቤቶች መታየት ይጀመራል።

በዓለም ሲኒማ
ኤድናሞል ሲኒማ
አምባሳደር ሲኒማ
እምቢልታ ሲኒማ

ዮፍታሄ ሲኒማ እንዲሁም በመላው አገሪቱ

በተመሳሳይ ሆኔታ የሁለት ጎራ
ሰለባ መሆናቸው ነው። በአንድ

በኩል በቅንጅቱ መሰባበር ምክንያት
ሲፈነድቅ የቆየው የወያነ ሥርዓት
የነዚህ ኃይሎች ተጠናክሮ መውጣት
አስደንግጦታል። በሌላ በኩል ደግሞ

በእነዚህ ኃይሎች መበለጣቸው
የተረዱ የተለያዩ የተቃዋሚ
ኃይሎች (ተቃዋሚዎችን ለመቃወም
የተቋቋሙ ተቃዋሚዎች ልንላቸው
እንችላለን) በተለያየ መንገድ
በአንድነት ፓርቲና በግንቦት-7
ንቅናቄ ላይ ሲዘምቱና አሉባልታ
ሲነዙ ይስተዋላሉ። ስለዚህ አንድነት
ፓርቲና ግንቦት-7 ከሁለት አቅጣጫ
ጦርነት እንደተከፈተባቸው መገንዘብ
ያስፈልጋል።

እንግዲህ የወ/ት ብርቱካን
ለዳግም እስር መዳረግ ስንፈትሽ
ይህንን ሁኔታ ታሳቢ በማድረግ
መሆን አለበት። ከዚያ በፊት
ግን የወያነ ሥርዓት አመራር
የሚፈራውን ኃይል ለማጥቃት ምን
ያህል ርቆ እንደሚሄድ እንመልከት።

ሥርዓቱ አንድን ተቃዋሚ
ግለሰብ ወይም ኃይል ሲያሳድድ
ካየን ተሳዳጁ ግለሰብ ወይም ኃይል
ለሥርዓቱ አስጊ ሆኖ ተገኝቷል
ማለት ነው። ለምሳሌ የግንቦት-7
መሪዎች በሌሉበት የሞት ፍርድ
ሲወሰንባቸው፤ ማየት ያለብን የፍርድ
ሂደቱን ሳይሆን ሰዎቹ ሥርዓቱን
የሚፈታተን አንድ ነገር በእጃቸው
ጨብጠዋል ማለት ነው። በተረፈ
ከውጭ አገር በሪሞት ኮንትሮል
መንግስት ሊገለብጡ ሞክረዋል ብሎ
መክሰስ አስቂኝ ኮሜዲ ካልሆነ ሌላ
ትርጉም የለውም።

በዚህ አጋጣሚ እኔም
አንዱ እማኝ ነኝ። በአንድ ወቅት
ሥርዓቱ እኔን በአስጊነት ፈረጀኝና
ወደ ተጠጋሁባት አገር (ዴንማርክ)
ድረስ ዘልቀው “በጦር ወንጀለኛነትና
በሰብዓዊ መብት ገፈፋ” የምፈለግ
መሆኔን ጠቅሰው ከሰውኛል። ይህን
ያደረጉት፣ ማንም ሰው ሊረዳው
እንደሚችል፣ እኔ በጦር ሜዳ ተገኝቼ
ሰው ስልገደልኩ ወይም የመንግስት

አቶ አብርሃም ያየህ

የብርቱካን የመኸር ጊዜ

በ ገፅ 20

ከህወሓት ጋር ተሰልፈው በኢትዮጵያ ታሪክ ተወዳዳሪ የሌለው ጀግንነት

የፈጸሙ ታጋይ ሴቶች (የታገሉለት ዓላማ ውሃ በልቶት መቅረቱ ቢያሳዝንም) ዛሬ

የትና በምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ እናውቀዋለን። በህወሓት ማዕከላይ ኮሚቴ ውስጥ

ስንት ሴቶች አሉ ተብሎ ቢጠየቅ መልሱ ምንም የሚል ሆኖ እናገኘዋለን።

Page 21

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 171 ቅዳሜ ሰኔ 04 2003ስ ፖ ር ት22

በአቤል ዓለማየሁ
[email protected]

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን
‹‹ለችግሮች ተገቢውን መፍትሔ የማይሰጥና ወጥ

አሰራርን የማይከተል›› ተብሎ ተተቸ

የፌዴራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት የ2002 ዓ.ም.
የበጀት ዓመት፣ የፌዴራል መንግስት መስሪያ ቤቶች ሂሳብ
ኦዲት ሪፖርት ከትላንት በስቲያ በህዝብ ተወካዮች ምክር
ቤት ባቀረበበት ወቅት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንን
የክዋኔ ኦዲት አስመልክቶ የተለያዩ ችግሮችን ዘርዝሯል፣
ማሳሰቢያም አቅርቧል።

የፌዴራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ዋና ኦዲተር
የሆኑት አቶ ገመቹ ዱቢሶ በሪፖርታቸው ላይ የኢትዮጵያ
አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የአትሌቲክስ ስፖርትን ለማስፋፋትና
ለማጠናከር ብሎም አገሪቱን ወክለው በተለያዩ ዓለም አቀፍ
እና በአህጉር ደረጃ በሚዘጋጁ የአትሌቲክስ ውድድሮች ላይ
የሚወዳዳሩ ተተኪ አትሌቶችን ለማፍራት በሁሉም ክልሎች
ከቀበሌ እና ከወረዳ ጀምሮ እስከ ክልል ድረስ ተገቢውን
ትኩረት ሰጥቶት ስፖርቱን ለማስፋፋት የሚያስችል
አደረጃጀት ባለማዋቀሩ በስፖርቱ ዙሪያ ለሚከሰቱ ችግሮች
ተገቢውን ወቅታዊ መፍትሔ የመስጠት ድክመት እንዳለበት
አስረድተዋል።

ዋና ኦዲተሩ ጨምረውም የታዳጊ እና ወጣቶች
ፕሮጀክት ስልጠና፣ ድጋፍ፣ ክትትልና ቁጥጥር የሚያደርጉ
የባለድርሻ አባላት አደረጃጀት ተግባርና ኃላፊነት በግልፅ
ያልተቀመጠ በመሆኑ ስፖርቱን በህብረተሰቡ ዘንድ
እንዲዘወተር እና እንዲስፋፋ ለማድረግ የተቀናጀና ወጥ
አሰራርን የተከተለ የአተገባበር ስራ በፌዴሬሽኑ ውስጥ
አለመቀየሱን ገልፀው ፌዴሬሽኑ ከሚመለከታቸው አካላት
ጋር ወቅታዊ መረጃዎችን በተገቢው መንገድ በመለዋወጥና፤
በመተግበር የተጠቀሱትን ችግሮች በማስወገድ አገሪቷ በዘርፉ
ልታገኝ የሚገባትን ውጤት ለማሳካት ጥረት ሊያደርግ
እንደሚገባ በሪፖርታቸው ላይ አሳስበዋል።

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዋና ስፖንሰሩን አስታወቀ
የተሳታፊዎች ቁጥር ይጨምራል •


ቀጣዩ ዓመት ለ11ኛ ጊዜ የሚካሄደው ዓለም አቀፋዊው
የታላቁ ሩጫ ውድድርን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና
ስፖንሰር መሆኑ ታወቀ።

ከትላንት በስቲያ በቬልቬት ሬስቶራንት በተሰጠው
ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ መስራችና
የቦርድ ዳይሬክተር ኃይሌ ገ/ሥላሴ እንደገለፀው በአሁን
ሰዓት በዓለም ላይ መሮጥ ካለባቸው አስር የሩጫ ውድድሮች
እየተባለ በዓለም መገናኛ ብዙሐን እየተነገረለት ያለው ይህ
ኢቬንት ስኬታማ የሆነው በሁሉም ባለድርሻ አካላት ርብርብ
መሆኑን ገልጾ ‹‹ማንኛውም ስራ እንደ ታላቁ ሩጫ ርብርብ
ከተደረገበት ሁሉም ነገር ይቻላል›› የሚል መልዕክት
አስተላልፏል። ውድድሩን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ስፖንሰር
በማድጉም ምስጋናውን አቅርቧል፤ ታላቁ ሩጫን ስፖንሰር
ማድረግ ተጠቃሚ እንደሚያደርግ በማስመር።

በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
የሰው ኃይል አስተዳዳር ምክትል ፕሬዚዳንት የሆኑት አቶ
ሰይፉ ቦጋለ ይህን የብዙዎች ትኩረት የሳበ የስፖርት መድረክ
ስፖንሰር በማድረጋቸው ደስተኛ መሆናቸውን በመግለፅ
‹‹ታላቁ ባንክ፣ ታላቁ ሩጫን ይደግፋል›› ብለዋል።

በተያያዘ ዜና ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ለታላቁ
የህዳሴ ግድብ ግንባታ ግማሽ ሚሊዮን ብር ቦንድ ከወለድ ነፃ
በእለቱ የገዛ ሲሆን የ100 ሺህ የገንዘብ ስጦታ ማበርከቱም
ተገልጿል። የታላቁ ሩጫ የተሳታፊዎች ቁጥር ባለፈው
ዓመት 35 ሺህ የነበረ ሲሆን ዘንድሮ ርግጠኛ መጠኑ
ለጊዜው ባይገለፅም ቁጥሩ እንደሚጨምር ታውቋል።

ኮፓ ኮካ ኮላ ወደ ሩብ ፍፃሜ ተሸጋገረ
በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች

መሀከል የሚካሄደው የኮፓ ኮካ ኮላ የእግር ኳስ ውድድር
ወደ ሩብ ፍፃሜ ተሸጋገረ። ዛሬ እና ነገ ወሳኝ ጨዋታዎች
ያደርጋሉ።

የአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽን፣ የአዲስ አበባ
ትምህርት ቢሮ፣ የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እና
ኢስት አፍሪካ ቦትሊንግ ሼር ካምፓኒ በጣምራ ያዘጋጁት
አራተኛው የኮፓ ኮካ ኮላ ውድድር በአዲስ አበባ እና
በድሬዳዋ ከተሞች እየተካሄደ የሚገኝ ሲሆን የድሬዳዋው
ነገ ድሬዳዋ አጠቃላይ እና ሳቢያን በሚያደርጉት የዋንጫ
ጨዋታ ፍፃሜውን የሚያገኝ ሲሆን ሰኔ 12 ይጠናቀቃል
ተብሎ የሚጠበቀው የአዲስ አበባ ውድድር ደግሞ ወሳኝ
ጨዋታዎችን ያስተናግዳል። በዚህ መሠረት ዛሬ እንጦጦ
አምባ ከቦሌ መሰናዶ፣ ከፍተኛ 23 ከዳግማዊ ሚኒልክ፣
አዲስ ከተማ ከሚሊኒየም እንዲሁም ነገ ደጃዝማች ባልቻ
ከአድቬንቲስት ጋር ወደ ግማሽ ፍፃሜ ለመግባት ይጫወታሉ።
የሴቶች ውድድር ወደ ጥሎ ማለፍ ተሸጋግሯል።

አራተኛው የኮፓ ኮኮ ኮላ ውድድር ሰኔ 19/2003
ዓ.ም. የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ አሸናፊ ቡድኖች በአዲስ
አበባ ስታዲየም በሚያደርጉት የአሸናፊዎች አሸናፊ ጨዋታ
ይጠናቀቃል።

ለተለያዩ አካላት እና
ግለሰቦች እንዲደርሱ በህትመት
መገናኛ ብዙሐን በኩል የሚላኩ
ጦማሮችን ሳነብ ኖሬያለሁ
እንጂ ይህን መሰል ጦማር
ለመስደድ ብዕር እና ወረቀት
ሳገናኝ የመጀመሪያዬ ነው።
እንደ አጋጣሚም የመጀመሪው
ለእርስዎ ሆነ፤ እንደምን አሉ
አቶ ሳህሉ ገ/ወልድ? ጠፉብን
እኮ!

መቼም እርስዎን
ለማግኘት በመደበኛነት
በሚሰሩበት ኮተቤ ኮሌጅ እና
ተመርጠው በፕሬዝዳንትነት
በሚመሩት የኢትዮጵያ እግር
ኳስ ፌዴሬሽን ቢሮ (አዲስ አበባ
ስታዲየም) ከመምጣት ይልቅ
ቦሌ ዓለም አቀፍ አይሮፕላን
ጣቢያ ቆሞ መጠበቅ የተሻለ
ነው እየተባለ እየተዜመ ያለውን
ዜማ ከጆሮዎ ሳይደርስ ይቀራል
ብዬ አልገምትም። ከሚመሩት
እግር ኳስ ፌዴሬሽን ስራ
በማስቀደም በኮሚሽነርነት
እየተመደቡ ተደጋጋሚ ጉዞ
ማድረግዎ የትችቱ የመጀመሪያ
ሀረግ እንደሆነም ይጠፋዎታል
ማለት ፊትን ጀርባ ብሎ
የመግለፅ ያህል ቀልድ ነው።
ሬዲዮውም፣ ጋዜጣውም
የእርስዎን ነገር እያነሳሳ
ቃላት እየወረወረ ነው፤ እኔም
ይሄው እዚህ ቁጥር ውስጥ
ተደመርኩ።

ከሁለት ዓመት
በፊት፤ ግንቦት 8/2001 ዓ.ም.
በሂልተን ሆቴል በዶ/ር አሸብር
የሚመራው የኢትዮጵያ እግር
ኳስ ፌዴሬሽን በጠራው
አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ
የፊፋ ልዑክ መሪና የሳይፕረስ
እግር ኳስ ፌዴሬሽን
ፕሬዝዳንት ሚስተር ኮስታኪስ
ኮትስኩምኒስን ጨምሮ
ሌሎች የልዑክ ቡድኑ አካላት
በተገኙበት አራት ንዑስ
አንቀጾች የተካተቱበት የዶክተር
አሸብርን አመራር የሚቃወም
ፅሁፍ ማንበብዎን [በወቅቱ
የደቡብ እግር ኳስ ፌዴሬሽን
ፕሬዝዳንት ነበሩ] ጉባዔውን
የታደምን የምንዘነጋው
አይደለም። የቀድሞው
ፕሬዝዳንት ራዕይ የሌላቸው፣
የውድድር ካላንደር በተገቢው
ሁኔታ የማያከብሩና ተፈፃሚ
የማያደርጉ፣ የክለቦችን አቤቱታ
የማይሰሙና የማይቀበሉ
መሆናቸውን፣ ለአዳጊና
ለወጣት ፕሮጀክቶች የሚሰጡት
ትኩረት አለመኖሩንና ከ14,850
በላይ አዳጊዎች የተካተቱባቸው
ፕሮጀክቶች እንደተዘጉ፣
በዶክተሩ የሚመራው ፌዴሬሽን
በአንድ አመት ውስጥ 12
የብሔራዊ ቡድን አሰልጣኞች
እንደቀያየሩ፣ ሰውዬው
አምባገነን መሪ እንደሆኑና
ተጨማሪ መረጃዎችን ሲዘረዝሩ
ከቤቱ ሞቅ ያለ ጭብጨባ
አግኝተዋል፤ ጉባዔተኛውንም
በደስታ አፍነክንከዋል። በወቅቱ
ከዘረዘሯቸው ውስጥ ብዙዎቹን
እኔም የማምንባቸው በመሆኑ
ያነበቡትን ሰነድ ቅጂ ከእጅዎ
ስቀበልዎት አልንገርዎ እንጂ
በሆዴ ‹‹ክብር ለእርስዎ›› ብዬ
ነበር።

ይህን ሁሉ ችግር
የደረደረ (ወይም እንዲደረደር
እድሉ የተሰጠው ሰው)
መልሶ ይህን ችግር ሲደግም
አነጋጋሪም፣ አስገራሚም
ይሆናል። እስቲ በቅንነት
ያስቡትና ራስዎን ይጠይቁ
‹‹ከዘረዘርኩት ውስጥ እኔ
ምን ያህሉን ቀርፌያለሁ?››
ብለው።

የውድድር ካላንደር
በተገቢው ሁኔታ አለመከበር

ዛሬም ድረስ የሚመሩት ቤት
ዋና ችግር ነው። ከሊጉ አቅም፣
ከአገራችን የኢኮኖሚም ሆነ
የእግር ኳስ ደረጃ አንፃር
በማይመጣጠን መልኩ በ16
ቡድኖች የሊግ ውድድር
በማድረግ ‹‹ክለቦች›› በውድድር
ማራቶን ይኸው እየዳከሩ
ነው። የኢትዮጵያ ጥሎ ማለፍ
ሻምፒዮና ሳይደረግ ተጨዋቾች
ከክለባቸው ጋር ያላቸው
የውል ዘመን መጠናቀቂያ፤
ሰኔ 30 ተቃርቧል። ሊጉንም
ቢሆን ቶሎ ለማጠናቀቅ ሲባል
ታላቆቹ የአውሮፓ ቡድኖች
እንኳን የማያደርጉትን ሃያ
ቀን በማይሞላ ጊዜ አምስት
ጨዋታ ለማድረግ ይገደዳሉ፤
ከሰኔ 1-19 ድረስ።

የአዳጊና ወጣቶች
ፕሮጀክትስ ቢሆን 24
ጣቢያዎች ከማቋቋም ባለፈ
የእርስዎ ካቢኔ ምን ሰራ?
ዛሬም ችግሩ እንዳለ ነው።
የቀያየሩት የብሔራዊ ቡድን
ቁጥር እንደቀድሞው ፌዴሬሽን
ደርዘን ባይሞላም ግልፅ ባልሆነ
ምክንያት መቀያየሩና መቅጠሩ
በእርስዎ ዘመንስ ተቀረፈ?
የአፍሪካ እግር ኳስ ስነ ልቦና
የማያውቁት፣ በአሰልጣኝነት
ይሄ ነው የሚባል ስራ ያልሰሩት
ስኮትላንዳዊው ኢፊ ኦኑራ ያለ
ባለሙያ መረጣ የተቀጠሩትና
‹‹ይሄ ነው›› ተብሎ ባልተገለፀ
ምክንያት የተባረሩት ይሄው
በእርስዎ ዘመን አይደለም
እንዴ? ለአምባገነንነትስ መች
መስፈርቱን ሳያሟሉ ቀሩና?
ጋዜጠኞች ሊያናግርዎት
ሲደውልሎት ጆሯቸው ላይ
መዝጋትዎን እርስዎ ባሉበት
ሲናገሩ ሰምቻለሁ። የአዲሱ
ኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን
አሰልጣኝ (ቶም ሴንትፌት)
ቅጥርን ከስራ አስፈፃሚ አባላት
ውስጥ ብዙዎቹ ሳያውቁ
መፈፀሙን በርግጠኝነት
አውቃለሁና ውሳኔዎችዎ
አምባገነናዊ እንደሆኑ አያሳዩም
ታዲያ? ነው ወይስ ጊዜዎ
በጉዞ ስለተጣበበ ለዚህ ማሰቢያ
ጊዜ የለዎት ይሆን?

የጉዞው ነገር
‹‹ባለፈው እሁድ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን
በአውሮፓ ታላላቅ ሊጎች
በሚጫወቱ ተጨዋቾች
ከተጥለቀለቀው የናይጄሪያ
አቻው ጋር በአዲሰ አበባ
ስታዲየም ተጫውቶ በመጨረሻ
ደቂቃ በተፈጠረ የእኛው ግብ
ጠባቂ የጊዜ አጠባበቅ ስህተት
ሁለት እኩል በተለያየንበት
ጨዋታ ላይ በስታዲየሙ
የተፈጠረውን እንባ ኩልል
የሚያደርግ አገራዊ ስሜት
እንዴት አዩት?›› ብዬ ጥያቄ
እንዳላቀርብልዎ በወቅቱ
እርስዎ መቼ በስታዲየሙም
ሆነ በአዲስ አበባ አልነበሩም።
በተለይ የናይጄሪያ እግር
ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት
የቡድናቸውን አባላት መርተው
አዲስ አበባ ሲገኙና የአቻቸው
ወንበር ስናይ ባዶ መሆኑ
አስደንግጦናል። እስቲ ያስቡት
ሰውዬው ‹‹አቻዬ የት ሄዱ?››
ብለው ሲጠይቁ ‹‹ለጨዋታ
ኮሚሽነር ሆነው ታንዛኒያ
ሄደዋል›› ማለት ምን ያህል
አሳፋሪ ነገር እንደሆነ።

አስቀድመው ትልቅ
ድግስ አለብኝ ብለው መቅረት
አሊያም ሌላ ኢትዮጵያዊ ሰው
መመደብ እየቻሉ በውሳኔዎ
መፅናትዎ ያስገርማል። እኛ
ኃጢያታቸውን የዘረዘሩት
ዶክተር አሸብር አንድ ቀን
በኮሚሽነርነት ሄዱ ሲባል
ሰምቼ አላውቅም። እድሉን
ያኔ ‹‹በኃጢያቱ›› ዘመን
በፌዴሬሽኑ ውስጥ ለነበሩት
እና ዛሬ የእርሰዎ ፌዴሬሽን
የፅህፈት ቤት ኃላፊ አድርገው
ለሾሟቸው አቶ አሸናፊ እጅጉና
ሌሎች ይጠቀሙበት ነበር።
ከ80 ሚሊየን ህዝብ በላይ
የወከለ የአንድ አገር እግር
ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት
አገራዊ ኃላፊነቱን ጥሎ
እንግዳ ለማስተዋወቅ ደረጃ
በመውጣትና በመውረድ ስራ

ላይ ተጠምዶ በአገር የለም
ሲባል ያሳፍራል። ክስተቱ
እርስዎ እግር ኳስን ለመጥቀም
ሳይሆን በእግር ኳሱ ለመጠቀም
እንደመጡ ፍንጭ የሚሰጥም
ይሆናል።

በእርግጥ እያንዳንዱ
የውጪ ጉዞዎ ቀላል የማይባል
ዶላር የሚዛቅበት መሆኑ እሙን
ነው። በአንድ ጉዞ ከ800 ዶላር
በላይ ኪሶ ይገባል። ይህ ማለት
እስካሁን ድረስ አድርገዋቸዋል
ተብሎ በሚገመተው 20 በላይ
ጉዞዎች ከሦስት መቶ ሺህ
ብር በላይ ኪስዎ ገብቷል
ማለት ነው። ይህን ያህል
ገንዘብ በሁለት ዓመት ውስጥ
የሚያገኝ የመንግስት ተቀጣሪ
ኢትዮጵያዊ የለም። ጠቅላይ
ሚኒስትሩ ‹‹ደሞዜ 6,400 ብር
ነው›› ካሉ በዲንነት በሚመሩት
ኮተቤ ኮሌጅ ለእርስዎ ይህንን
ያህል እንደማይከፍልዎ
እገምታሁ። የተጠቀሰው
ገንዘብ (የካፍ የአበል ክፍያ)
ከፍተኛ መሆን ሊያጓጓዎ
ቢችልም አስቸኳይ ጠቅላላ
ጉባዔ ሰውን ያወገዘ ሰው
በእርስዎ እንዳይደርስ ጥንቃቄ
ሊወስዱ በተገባዎት ነበር።
እያደረጉት ያለው ክስተት ግን
ከዚህ ተቃራኒ መስሎኛል።
የገንዘብ ጉጉ እንዳይሆን
ገንዘባዊ አቅሙ ጠንካራ የሆነ
ሰው ወደ ፌዴሬሽኑ ሊመጣ
እንደሚገባው ሊታሰብበት
የሚገባ አንኳር ጉዳይ
ይመስለኛል። ይህን ስል እንደ
ቀድሞ አቻዎ ዶክተር አሸብር
አይነቱ ገንዘብ ስላለው ብቻ
ይምጣ ማለቴም አይደለም፤
ገንዘብ ሲደመር እግር ኳሳዊ
ፍላጎትና እውቀት ይታከልበት
ማለቴ ነው። እርስዎ
ከዚህ ውስጥ ምን ያህሉን
እንደሚያሟሉ እኔ እንጃ!

ተዳፍኖ የቆየው
ተግባርዎ በትልቁ ድግስ እለት
(የናይጄሪያ ጨዋታ ላይ) ገኖ
ወጣ እንጂ የጉዞ ውጥረት
ውስጥ ከገቡ እንደሰነበቱ
ሳናውቅ ቀርተን አይደለም።
በእለቱ ሰንደቅ ዓላማውን
አንግቦ ከስፖርታዊ ጨዋነት
ዘጠና ደቂቃ ድጋፍ የሰጠ ህዝብ
በሳምንቱ አጋማሽ በአዲስ
አበባ በተካሄዱ የፕሪምየር
ሊግ ጨዋታዎች ላይ
ለአገሩ በዘመረበት አንደበቱ፣
በእርስዎ ላይ የተቃውሞ
ድምፅ ሲያሰማ ነበር። መገናኛ
ብዙሐንም ‹‹አንደኛቸውን
ጠቅልለው ካፍ ይግቡ›› ሲሉ
እስከ መተቸት ያደረሳቸው

የእርስዎ ደጋግሞ አየር ላይ
መንሳፈፍ የአገርን እግር ኳስ
ከመጥቀም ይልቅ ኪስዎን
እንደጠቀመ በማሰብ ነው።
ህዝቡ ዝናም ‹‹እየቀጠቀጠው››
ለአገሩ ብዙ ሲያዋጣ፣ የድግሱ
መሪ ግን የራስዎን ገፍተው
በሰው ድግስ ላይ ሲያስተናብሩ
መዋል በርካታ ባለድርሻ
አካላትን አሸማቋል፡፡ እርስዎን
‹‹ምሩኝ›› ብሎ ያስቀመጥዎት
ክለቦች፣ የክልል መስተዳድር
ፌዴሬሽኖች እና የሌሎች
በጠቅላላ ጉባኤ ላይ ድምፅ
ያላቸው አካላት ዝምታም
አስገርሞናል። ዝምታቸው
እርስዎንስ አላስገረምዎትም?

ከክስ፤ ኃላፊነትን
መወጣት ይቅደም!

በፌዴሬሽን ውስጥ
ያላችሁ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ
አባላት እያንዳንዳችሁ በስራችሁ
የምትመሩት ኮሚቴ አለ።
እርስዎም የህክምና ኮሚቴ
ሰብሳቢ መሆንዎ ይታወቃል።
ይህ ‹‹ኮሚቴ›› ግን ደካማና
አለ ለማለት አስቸጋሪ እንደሆነ
በዙሪያዎ ያሉ ይገልፃሉ፡
፡ ኮሚቴውንም በአግባቡ
መሰብሰብ አለመቻልዎን
ሰምቻለሁ፤ በተጨባጭም
ታይቷል።

ባለፈው ወር ሙገርና
ደደቢት በአዲስ አበባ ስታዲየም
ባደረጉት ጨዋታ ላይ የሙገሩ
ተከላካይ ዳንዔል መኮንን
በግጭት ጉዳት ደርሶበት፣
ምላሱን ውጦ ህይወቱ
ሊያልፍ ሲል አንድም እርስዎ
የሚመሩት የህክምና ቡድን
አባል በስታዲየሙ ተገኝቶ
ሊረዳው አልቻለም። የዚህ
ልጅ ህይወት አልፎ ቢሆን
ኖሮ የህክምና ባለሙያና
ረጂ መሳሪያዎችን ማቅረብ
ያልቻለው ለስም ብቻ ያለው
የህክምና ኮሚቴና [በዋናነትም]
እርስዎ ተጠያቂ ይሆኑ
እንደነበር ያውቁታል? አሁንስ
ይህ ጉዳይ አሳስቦት ከውጪ
ጉዞዎ ላይ ቀንሰው ጊዜ
ሰጥተውት እያሰቡበት ነው?

በባህር ዳሩ የጠቅላላ
ጉባኤ ላይ አድንቀዋቸው
‹‹ቤቱ አላሰራ አለኝ››
ብለው መልቂያ ካስገቡ
በኋላ ፌዴሬሽኑ በቸርቸል
ቪው ሆቴል በተሰጠው
ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ግን
ምንም እንዳልሰራ የተቹትን
የቀድሞውን የፌዴሬሽኑ
ቴክኒካል ዳይሬክተር (አቶ
ዮሐንስ ሳህሌ) የፌዴሬሽኑን
ችግሮች አስመልክቶ በፋና
ብሮድካስት ግንቦት 8/2003
ዓ.ም. በሰጡት አስተያየት ሳቢያ
ባለፈው ማክሰኞ የፌዴሬሽኑ
ዲስፕሊን ኮሚቴ ጠርቶ
አነጋግሯቸዋል። የክሱ ጠንሳሽ
እርስዎ ስለመሆንዎ መረጃ
ሰብስቤያለሁ። ትክክል ነው /
አይደለም ለማለት ባልፈልግም
በእለቱ የአቶ ዮሐንስን ገንቢ
ትችት ተከታትየዋለሁ። በተለይ
ፌዴሬሽኑ በባለሙያዎች

መመራት እንዳለበት ደጋግመው
ሲያስገነዝቡ ነበር። ማንም ሰው
ደግሞ አመለካከቱን እና ሀሳቡን
በነፃ የመያዝና የመግለፅ
መብት እንዳለው በኢትዮጵያ
ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ
ሪፐብሊክ ሕገ-መንግስት
አንቀጽ 29 ላይ የሰፈረ ነው።
በዚህ አንቀጽ ‹‹ለ›› ላይ
‹‹ማንኛውም ሰው ያለ ማንም
ጣልቃ ገብነት … በመረጠው
ማንኛውም የማሰራጫ ዘዴ
ማንኛውንም ዓይነት መረጃና
ሐሳብ፣ ሙያዊ አስተያየት
የመሰብሰብ፣ የመቀበል፣
የማሰራጨት ነፃነቶች መብት
ይኖረዋል›› ይላል። ይህ አንቀፅ
ተማምነን ነው እኔና ሌሎች
የሙያ ጓደኞቼ ሀሳባችንን
እንድንገልፅ የሚያደርገን። እናስ
እርስዎ እና ፌዴሬሽንዎ ይሄን
ተገንዝባችሁ ጠቃሚውን ሀሳብ
ወስዳችሁ የማይጠቅመውን
መጣል ሲገባችሁ ለክስ
መፍጠናችሁ አስገረሞኛል።
ምነው ይሄን ፍጥነት እግር
ኳሱን ለመርዳት ብታውሉት
አስብሎኛል።

አቶ ዮሐንስን መክሰስ
የሚያስተላልፈው መልዕክት
እንደ አገርም ጎጂ መሆኑን
እንዲያጤኑት ከሰሙኝ
ወንድማዊ ምክሬን ባካፍሎት
ደስተኛ ነኝ። እንደሚያውቁት
እኚህ ባለሙያ መኖሪያቸውን
ባደረጉበት አሜሪካ እና
በተለያዩ አገሮች ተንቀሳቅሰው
ያካበቱት ልምድ ከኢትዮጵያ
የእግር ኳስ ቁመት በላይ ነው።
አገራቸውን ለመርዳት ወይም
በአገራቸው ላይ ለመስራት
መጥተው እሳቸው እንደገለፁት
አመቺ የስራ ክበብ በፌዴሬሽኑ
አልገጠማቸውም። አሁን
ደግሞ ‹‹ሰጡት›› በተባለው
አስተያየት ክስ መሰናዳቱ
ሌሎች በውጪ አገር የሚገኙ
ኢትዮጵያውያን አገራቸው
ገብቶ መስራት ያለውን
ተግዳሮት ጉልህ ማመላከቻ
ስለሚሆን አገራቸው ገብተው
መስራት ይፈራሉ። ‹‹በውጪ
ያሉ ኢትዮጵያውያን ባላቸው
አቅም አገራቸውን የሚረዱበት
አቅም ተመቻችቷል››
እየተባለ በሚደሰኮርበት
ወቅት ይህ እርስዎ የመሩት
ክስ የሚባለው ሁሉ ውሸት
መሆኑን ስለሚገልፅ ለአገር
ያለውን ጉዳት ሊያጤኑት
ይገባል። [ይህ ማለቴ ግን
ያጠፋ አይገሰፅ ማለቴ
አይደለም] ለክስ ከመትጋትዎ
በፊት ኃላፊነትዎን በአግባቡ
መወጣትም ላይ ትኩረት
ይስጡ።

ከስንብቴ በፊት…
የኢትዮጵያ እግር

ኳስ እንደሚያውቁት በችግር
የተተበተበ ነው። ችግሮቹ
ሁሉ ለቅሞ ጥሎ የሚጨርስ
ባለሙያ ማግኘት ቀርቶ
እንኳን ችግሩን የሚያቀል ሰው
ፍለጋ ላይ በሚዳክርበት ወቅት
ጥሩ ፕሬዝዳንት እንዳላገኘ
የዘረዘርኳቸው ምሳሌዎች
ጥሩ ማረጋገጫዎች ናቸው፤
ይህን እየቆመጠጥዎትም
ቢሆን ሊጎነጩትና ሊያምኑት
ይገባል ብዬ አምናለሁ።
ተቃውሞ ከሁሉም ቦታ
በርክቶቦታል። ይህ የጭለማ
ጊዜ አልፎ ጭላንጭል
ብርሃን ለመመልከት በብርሃን
ፍጥነት በመንቃት ስህተትዎን
ለማረም ተግተው ካልሰሩ
በአስቸኳይ የጠቅላላ ጉባዔ
ላይ ምስክርነት ያነበቡት ሰነድ
በእርስዎ የሚነበብበት ጊዜ ሩቅ
እንደማይሆን አምናለሁ።

በቅርብ የሚያውቆት
ጥሩ አስተማሪ እንደሆኑ፣
የታመቀ የመስራት አቅምና
መጥፎ የማይባል ግለሰባዊ
ባህሪ እንዳለዎ ይገልፃሉና
ይህን ዙሪያ ገባውን ቃኝተው
‹‹ምን እየሰራሁ ነው?››
ብለው በመጠየቅ ለመንቃት
ይጠቀሙበት፡፡ ትችታዊ
ጦማሬን በበጎ እና በቅንነት
ይውሰዱት። መልካም የስራ
ጊዜ ይሁንልዎ።

ይድረስ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት

ወደ ፌዴሬሽኑ የመጡት ራስዎን ወይስ እግር ኳሱን ሊጠቅሙ?

የዚህ
ልጅ ህይወት አልፎ

ቢሆን ኖሮ የህክምና
ባለሙያና ረጂ

መሳሪያዎችን ማቅረብ
ያልቻለው ለስም

ብቻ ያለው የህክምና
ኮሚቴና [በዋናነትም]
እርስዎ ተጠያቂ ይሆኑ
እንደነበር ያውቁታል?

አሁንስ ይህ ጉዳይ
አሳስቦት ከውጪ ጉዞዎ

ላይ ቀንሰው ጊዜ
ሰጥተውት እያሰቡበት

ነው?

Page 22

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 171 ቅዳሜ ሰኔ 04 2003

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

23

}SdeK¨< Ÿ}c\ ð×” ¾h¨` ¨<H TVmÁ
U`„‹ ÃÖ”kl ƒ¡¡K—¨<” ¾w^²=M

¾h¨` ¨<H TVmÁ ÃÖkS<

Brazmart International General Trading Plc.
Address!- • Urail Alem Brehan Plaza 1st Floor #106

1. ›<^›?M u?} ¡`e+Á” ›”vu= ¯KU w`H” ýL³ 1— öp u=a lØ` 106
2. Ku< ›Åvvà òƒ Kòƒ dS<›?M I”í
uT”—¨<U ¾vD”vD“ ¾h¨` u?ƒ �n ዎ ‹ SgÝ“ �”Ç=G<U u¾I”í SX]Á SÅwa‹ ÁÑ–<�M::

c=Ѳ< ƒ¡¡K— ¾w^²=M U`ƒ SJ’<” Á[ÒÓÖ<!
Tel. 251-11 552 -6011 /12 Fax 251-11-5526012

ሰፋ ብሎ ውሃ
የሚያወርድ

ምቾት እና
ጥራት ያለው

ከበቂ
መለዋወጫ ጋር

ለጥንቃቄዎ
የተመሳሰሉትን

ይለዩ

ምን እየተሰራ ነው?
ባህላዊ የትምህርት

አሰጣጦችን በዘመናዊ ለመተካት
ጥንታዊ አሰራሮችን በአዲስ
መልክ ለማዋቀር ጊዜ ቆጣቢ
አገልግሎቶችን ለማስፋፋት ምን
ጥረት እየተደረገ ነው?

ነገሮች አሁን ባላው
መልኩ ከቀጠሉ ከጥቂት ዓመታት
በኋላ ኢትዮጵያ የራሷ ስለሆነው
ፊደልመ፣ ያሬዳዊ ዜማ፣ ፅናፅል፣
ከበሮ ወዘተ የማውራት አቅሟን
እንደምታጣ አጥታችሁት ነውን?

ለዚች አገር
እንደቤተመጽሐፍት የሚቆጠሩ
ግለሰቦች አንድ ባንድ በእርጅና
በእረፍት እስኪለዩን የምንጠብቀው
ለምንድን ነው? በግራም ነፈሰ
በቀኝ የነሱ ዕውቀት እና ችሎታ
ለዚች ሀገር ሥልጣኔ የራሱ የሆነ
አስተዋጸኦ ይኖረዋል። ይህንንም
ከትናንት ይበልጥ ዛሬ ከዛሬም
ይበልጥ ነገ ማስመስከር መቻል
የአገርን ግዴታ መወጣት ነው።

በሀገሪቱ በዓለማዊ
ትምህርት ውስጥ የማይገኙ
ባህረ-ሐሳብን (የቀን አቆጣጠር
ትምህርት) የመሳሰሉ ትምህርቶችና
ቀመሮች ለዚች አገር ተጠብቀው
መቆየት የለባቸውም ወይ?

ይህንን ያስተዋሉ አንድ
የቤተክርስቲያኗ ሰባኪ በአንድ
ወቅት በየገጠሩ እየተንከራተቱ
ብዙ ቀለም የቀሰሙ ምሁራን
የሳንቲም መሰብሰቢያ ሳጥናቸውን
አውርደው በማዕከላት ውስጥ
የሚያገለግሉበት አሰራር ይፈጠር
ሲሉ ድምፃቸውን አሰምተው
ነበር።

እኔም በግሌ የኢትዮጵያ
ኃብቶች እየተባሉ የሚጠሩ
ነገሮች መሠረታቸው ይችው
ቤተክርስቲያን ስለሆነች በየጊዜው
አዳዲስና ቀልጣፋ የማስተማሪያ
ሥነ-ዘዴዎችና መዋቅሮችን
ተቋማትንና ቴክኖሎጂን መጠቀም
ተገቢ ይመስለኛል።


መሪዎች /መምህራን/

ፍፁም አንዲሆኑ እንኳ ባይጠበቅ
ምሉዕ ሊሆኑ ግድ ነው።
በቤተክርስቲያኗ ብቻ ሳይሆን
በሀገሪቱ፣ በሀገሪቱ ብቻ ሳይሆን
በዓለም የሰላም አባት ተብላችሁ
የምትጠቀሱ አባቶች እውን የሰላም
አባት ነን ብላችሁ ታስባላችሁ?
ካሰባችሁስ እንደሆናችሁ እርግጠኛ
ናችሁ?

ለዚህ ህዝብ ምንድንነው
የምናስትምረው? ምንን
እየተናገርን ምንን እየኖርን ነው
አርአያ የምንሆነው? ጥለነው
ወጥተናል በምንኩስና ተለይተናል
ከምንለው ዓለም መራቃችንን
ዘወትር በጭቅጭቅ በግብግብ
በንዝንዝ በኩርፊያ ነው እንዴ
የምንገልፀው?

ከዓመትና ከኹለት ዓመት
ወዲህ የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ
ሲቃረብ የመካከለኛው ምስራቅ
ቀውስ ይመስል ደግሞ ዛሬ ምን
ይመጣ ይሆን እየተባለ ይጠበቃል።
ይሄ በመንፈሳዊ ቤት ይሄ የሀገርን
አደራ በተሸከሙ አባቶች ዘንድ
የሚጠበቅ ነበር?

እርስ በርሳችሁ
እየተተረማመሳችሁ መደማመጥ
እየተሳናችሁ እያየን በሚዲያ
ስለፍቅር ብትሰብኩን ሊገባን
ይችላል? በዓለማዊ መንግስት
ውስጥ የታከቱንን አሰራሮችና
ሸፍጦች ሰርተሃል አልሰራሁም
እያላችሁ አተካሮ ስትገጥሙ
እየተመለከትን ስለቅንነት
ብትናገሩን እንዴት ብለን
እንረዳለን?

ዋጋን የሚወስነው የዓለም የገበያ ዋጋ ነው። ነገር ግን የሥነ-ፅሁፍ
ሙያን ለማበረታታት መንግስት ሊወስዳቸው የሚችሉ አንዳንድ
እርምጃዎች ይጠፋሉ ለማለት ግን ይቸግራል። ይህን ማድረግ ካልተቻለ
ግን ሕገመንግስቱ ለሕዝቡ የሰጣቸው በርካታ የባህል መብቶች ከቶም
ሊተገበሩ አይችሉም። በመንግስት የሚተዳደሩት የመገናኛ ብዙሃን እንኳ
ለሥነ-ፅሁፍ በአጠቃላይም ለሥነ-ጥበብ ያላቸው ትኩረት እጅግ አናሳ
ነው።

በመድረኩ ላይ ከተነሱት ጥያቄዎች አንዱ ለሥነ-ጥበቡ
ክብር የሚሆን አንድ ዓመታዊ ቀን እንዲሰየም ነበር። ይህ መልካም
ሀሳብ ሲሆን ነገር ግን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለተባለው የመታሰቢያ ቀን
በዚሁ መድረክ ላይ እውቅና እንዲሰጡ በጭብጨባ ጫና ማስገደዱ
ተገቢ ያልሆነ አካሄድ ነው። ለጥያቄው በተሰጠው ምላሽም ጉዳዩ በዚህ
መልክ የሚወሰን እንዳልሆነ ተገልጿል። በእኔ አመለካከት የሥነ-ጥበብ

መፈረጅንና መጠቆርን ሳንሰጋ
በቅንነት የሚሰማንን ተነጋግረን
መግባባት ላይ የምንደርስበት፣
የሚለያዩ የጓዳና የአደባባይ
ማንነቶች ማበጀት የማያስፈልግበት
ዘመን የሚመጣው መቼ ነው?››
ብሎ መጠየቅ የዋህ ያስብለን
ይሆን?

መ ረ ዳ ታ ች ን
የፈቀደልንን ያህል ስንገነዘበው
አንድን ሁነት ተከትለው
የሚያጎነቁሉ ሁሉንም አይነት
አፀፋዎች አንደማስተናገድና
ለመመርመር እንደመትጋት
የተመረጡ የተወሰኑትን ይዞ፣
ለቀሩት ቦታና እድል ነፍጎ
የቆመ አሰራር ህዝብን ያማከለና
የሚያነቃንቅ ሊሆን አይችልም።
ምናልባት ሁሌም የሚገባንን (‹‹ገ››
ጠብቆ ይነበብ) የሚመርጡልን
አካላት ተገቢ ነው ብለው
ያመኑበትን ሀሳብ ሁላችንም
እንድናምንበት እስክንደነቁር ድረስ
በማስጮህ ሌሎች እሳቤዎችን
ጨፍልቆ ለማስቀረት አሊያም
ከትኩረት እንዲሰወሩ ለማድረገ

ያስችል ይሆናል። ግን ነገሩ ‹‹ሆድ
ሲያውቅ ዶሮ ማታ›› ነውና በኋላ
አፋችንን ሞልተን አንድ ላይ
ሆነን ይሄን አደረግን›› ለማለት
እንቸገራለን።

እነኚህን መሰል ሰፊ
ተሳትፎ የሚጠይቁ ታላላቅ
አጋጣሚዎችን ታክከው
የሚደመጡ ተዳፍነው የከረሙበትን
አመድ አራግፈው ያልጨረሱ ሆድ
ብሶቶች አሉ። ‹‹ተዘንግተን የኖርን
ሰዎች ዛሬ እንደምን ታወስን?››
አንዱ ነው። እፍ ያለ ፍቅራቸውን
አሟጠው ብው ያለ ጠብ ውስጥ
የተገኙት ኢትዮጵያና ኤርትራ
ጦርነት በደራበት ወቅት በተደረጉ
ውይይቶች/ስብሰባዎች ደጋግሞ
ተነስቷል። ሥራ-አጦች ‹‹ኑሮን
መጋፈጥ ከብዶን የምንሆነው ስናጣ
ችግራችንን ሳትቀርፉ የተገኘውን
ሥራ ሁሉ ለካድሬዎቻችሁ
ስትነዙ ቆይታችሁ ትዝ ያልናችሁ
የሚጠበቅብን ሲኖር ብቻ ነው?››
ብለዋል። ከገበሬ ወላጆች የተገኙ
ተማሪዎች ወላጆቻቸውን በሚያገል
መንፈስ ሲበግኑ መንግስት የት

እንደነበር አፋጠዋል። መንግስትን
ወክለው የሚያወያዩ ባለስልጣናት
ይሰጡት የነበረው ምላሽ ዜጎቿን
አበላልጣ የምትመዝን አገር መኖር
እንደማይገባት የሚያሰረግጥ፣
ስህተት ካለም መታረሙ
እንደማይቀር ተስፋ የሚሰጥ ጥሪ
ነው። ይሄው ዛሬ ደግሞ አባይ
ሆድ ብሶቶቹን ደግሞ ለፀሀይ
አብቅቷቸዋል።

ሰዎች ዜግነታቸው
እውቅና የሚሰጠው የሚፈለግባቸው
ነገር ሲኖር ብቻ መሆን የለበትም።
ዘመን ሞቶ ሌላ ዘመን በተወለደ፣
ትኩሳት በርዶ ሌላ ግለት መሟሟቅ
በጀመረ ቁጥር የማይቀር ጉንጭ-
አልፋ ንትርክ ካለ ያልተሰራ
ሥራን አመላካች ነው። እስከመቼ
ቀጣይነት እንደሚኖረው መገመት
ይከብዳል። ብቻ ሁሉም በሮች
ያለአድልኦ እኩል ተከፍተው
እንደችሎታችንና ፍላጎታችን
የምንገባ የምንወጣበት እለት ቶሎ
እንዲመጣ እንመኛለን። ለልማትም
ሆነ ለሌላ ሀገራዊ ጥሪ ሆ ብሎ
መነሳት ያኔ ይቀለናል።

ሙያተኛው ‹‹ክብር ለጥበብ›› የተባለውን እለት በራሱ ሰይሞና በተለያዩ
ትዕይንቶች ማክበር ጀምሮ የመንግስትን ይፋዊ እውቅ መጠየቅ የሚቻል
ነው። ይህ ሥራ ከራሱ ከጥበብ ቤተሰቡ መጀመር ያለበት ነው። አባቶች
ሲተርቱ ‹‹ባለቤቱ ያቀለለውን ባለዕዳ አይቀበለውም›› እንዲሉ።

በመድረኩ ላይ አብላጫዎቹ ጥያቄዎች የቀረቡት ከኪነ-ጥበብ
ሙያተኛው የእለት ከእለት ችግሮችና ወቅታዊ ተግዳሮቶች አኳያ ነበር።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሰጡት ምላሽ ግን አሁን ያሉትን የእለት ችግሮች
የተመለከተ ሳይሆን የመንግስትን አጠቃላይ ፖሊሲ፣ ለመጪው ዘመን
የሥነ-ጥበብ እድገት የሚያስፈልጉትን መሰረተ ልማቶች የተመለከቱ
ሀሳቦች ላይ ነበር። ‹‹መንግስት የልማት አጀንዳውን ለማስፈፀም የሥነ-
ጥበብ ሚናን ይፈልገዋል›› ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሥራውን ቅደም
ተከተል በማውጣት መንግስት ባለው ውስን የሰው ኃይልና የፋይናንስ
አቅም በጋራ ለመስራት የሚችል መሆኑን ገልፀዋል። እንዳሉትም

መንግስት በሥነ-ጥበብ ይገለገላል። ሥነ-ጥበብን የሚገለገል ከሆነ ደግሞ
የሥነ-ጥበብ ህመሟን፣ ችግርና ጉዳቷን አብሮ ሊጋራው ይገባል።
የአገሪቱ ከያንያን ሥራና ሕይወት እንደፕላስቲክ መጠጫ ‹‹use and
throw›› ሆኖ መቀጠል አይገባውም።

በአንድ በኩል እራሱ የሥነ-ጥበብ ሙያተኛው መራመድ
የሚችለውን ያህል አልተጓዘም። በሌላ በኩል ደግሞ መንግስት በሥነ-
ጥበብ ላይ ያለውን የቤት ሥራ በአግባቡ አልተወጣም። የመንግስት
አስተዳደር ሊኮራ የሚገባው በከተማ ውስጥ በተገነቡ ፎቆች ብዛት
ወይም በገጠር በዘረጋቸው መንገዶች ብቻ አይደም። መንግስት ለአገሩ
የሥነ-ጥበብ እድገት ምን አስተዋጽኦ አበርክቷል? ባህል ነክ ዓላማዎችን
በሕገመንግሰቱ ከማስፈር በተጨማሪ መብቶቹን በተግባር ለመተርጎም
ምን ያህል እየሰራ ነው? የጥበብ ቤተሰቦች ሕይወት እንዴት ያለ ነው?
የሚሉ መለኪያዎችም አብረው ይነሳሉ። በድራማው ላይ እንደታየው
የሥነ-ጥበብ ሙያተኞች መራብ፣ መጠማት፣ መዘረፍና ከሀገር መሰደድ
መንግስትን በእጅጉ ሊያሳስበውና ሊያነቃው ይገባል። ፈላስፋው ኦሻ
እንደሚለው ደግሞ ‹‹ከልብ ካዳመጣችሁት የውሻ ጩኸትም የቡድሀ
ጥሪ ሊሆን ይችላል። ከልብ ካላደመጣችሁ ግን የቡድሀ ጥሪም የውሻ
ጩኸት ነው።››

መጽሐፉ እንዲህ ይላል፡
- ‹‹የአምላካችንን ሕግ አድምጡ።
የመስዋዕታችሁ ብዛት ለእኔ ምን
ይጠቅመኛል? ይላል እግዚአብሔር
… ታጠቡ ሰውነታችሁንም አንፁ
የሥራችሁንም ክፋት ከዐይኔ ፊት
አስወግዱ። ክፉ ማድረግን ተዉ።
መልካም መሥራትንም ተማሩ።
ፍርድን ፈልጉ የተገፋውን
አድኑ ለደሃ አደጉ ፍረዱለት
ስለመበለቲቱም ተሟገቱ››

ት. ኢሳይያስ 1፤10 -18
እናንተ ግን በተቃራኒው

እንደሆናችሁ ሚዲያዎች ያወራሉ።
የደነደነ ልብ ይዛችሁ ስለምትመሩት
ህዝብ ሳትጨነቁ በእግዚአብሔር
ቤት ትፎካከራላችሁ።

እኛ’ኮ ከእናንተ
የምንጠብቀው ይህንን አይደለም።
ዓለማዊ መንግስታችን ሲበድለን፣
ሲጨቁነን፣ ሲያንገላታን
መክራችሁና ያገባናል ብላችሁ
የልጆቻችንን ለቅሶ ይሰማናል
ብላችሁ እንድትቆሙልን፣ መአት
ቢመጣ እንድትፀልዮልን በሽታ
ቢመጣ እንድታማልዱን እንጅ
በየጉባኤው እየተኮራረፋችሁ
የሚዲያ ሲሳይ እንድትሆኑ
አልነበረም።


የኢትዮጵያ ህዝብ

የውስጡን ችግር የሚፈታለት
የሚያስተባብረው አካል እስካገኘ
ድረስ ለመተባበር የቆረጠ እንደሆነ
በተለያየ አጋጣሚ አስመስክሯል።
ይህንን ቢያንስ አሁን እየተባበረበት
ባለው የአባይ ግድብ ግንባታ ማየት
ይቻላል።

ማስተባበርም ሲባል
ቀዳሚውንና ተከታዩን ለይቶ
የሚጠቅመውንና ፈጣኑን ዘዴ
መስርቶ ‹እባክህ› በማለት ማነሳሳት
ነው። የቤትክርስቲያኗ አባቶች
በዚህ በኩል እንዴት ናችሁ?
በየቤተክርስቲያኑ አጥር የወደቁ
ተመፅዋቾችን አንስቶ በማቋቋም፣
የታመሙትን በመርዳት፣ ያዘኑትን
በማፅናናት ምን እየተደረገ ነው?

ቤተክርስቲያኗ እንደሀገር
መስራት ያለባት ይመስለኛል።
አባቶች የሰማኒያ ሚሊየን ህዝብ
ኃላፊነት በላያችሁ አለ። የህፃናት
መረጃ ያረጋዊያን ማቋቋሚያ
እየተባለ ስም ከሚለጠፍላቸው
ማኅበራት በዘለለና በገዘፈ መልኩ
መንቀሳቀስ ያለበት ይመስለኛል።

አንዳንዶችን የሚያስቆጣ፣
አንዳንዶችን የሚያስደስት፣
ብዙዎችን ግራ የሚያጋባ ፎቶግራፍ
ከመስቀልና ሐውልት ከማቆም
በፊት ቅድሚያ የሚሰጣቸው
የኢትዮጵያውያን ማኅበራዊና
ኢኮኖሚያዊ ችግሮች አሉ።

እርግጥ እያነሳኋቸው
ያሉ ጉዳዮችን የቤተክርስቲያኗ
ኃላፊነቶች አይደሉም የሚል
ተራ መከራከሪያ ሊነሳ ይችላል።
እንዲሁም በግርድፉ ስናየው
የመንግስት ብቻ ኃላፊነቶች
ይመስሉ ይሆናል። እኔ ግን እላለሁ
ያነሳኋቸው ነገሮች ከማንም በፊት
የቤተክርስቲያን ኃላፊነቶች ናቸው።
አዎ! የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ
ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ኃላፊነት!

ቤ ተ ክ ር ስ ቲ ያ ኗ
የምታስተምረው ‹‹ተርቤ ነበር
አበላችሁኝን ተጠምቼ ነበር
አጠጣችሁኝን ታስሬ ነበር
ጎበኛችሁኝን (ማቴ 25 - 15)
ትምህርቶች ሁሉ ቃላዊ ሆነው
የትም እናገኛቸዋለን። ተግባራዊ
ሆነው ግን በዚች ቤተክርስቲያን
ማግኘት አለብን።

ትናንትና አንድ የራበው
የኔቢጤ የቤተክርስቲያን አጥር
ተደግፎ ሲያንቀላፋ ስላላስተዋልነው

ዛሬ ዛሬ በየቤተክርስቲያኑ የኔ
ቢጤዎች ሲርመሰመሱ ብናይ
አልገርመን አለ። ትናንትና
ምዕመናን ስለሚያቀርቡት
መክለፍት እና መሀራ ግልጥ
ያለ ደንብ ስላላወጣን ጠላና አረቂ
ብሎም ቢራ (አሁን አሁን ደግሞ
እንደምንሰማው ጉቦ) መጠየቅ
ሲታይ አላስደነግጠን አለ።

የነፍስ አባት ለመሆን
የምዕመኑን የገቢ መጠን
የሚያጣሩ ካህናት እንዳሉ ሰምተን
አናውቅምን? በመንግስት መስሪያ
ቤት አካባቢ እያየነው የሚቀፈን
የብሔር ጉዳይ የሚያነሱ እንዳሉ
አልሰማንምን?

እኒህና እኒህን የመሰሉ
ቅድሚያ ሊሰጣቸው ሲገባ ተቀጥላ
ለሆኑ ተግባራት ቅድሚያ ሲሰጥ
ማየት ደስታ አያጭርም።

ሀገራዊ ማንነትንና
አንድነትን ብሎም የጋራ መገለጫን
መገንባት የሚቻለው በእምነትና
በእውነት ነው። እምነትም
እውነትም የቤተክርስቲያኗ
አስተምህሮዎች ናቸው። ከእነዚህ
ትምህርቶች የሚጣረሱ ተግባራት
ደግሞ በቤተክርስቲያኗ ዙሪያ
በቅለው ሲገኙ ያስቆጫል።
ማንነትን አስመልክቶ ቅርሶች ነዋየ
ቅዱሳት ጠፉ፣ ተሸጡ፣ ተመዘበሩ
ወዘተ ይባላል። ከእነዚህ ችግሮች
ፊት ግን የቤተክርስቲያኗን
ምስጢር የሚያውቁ አገልጋይ
ካህናት ይገኛሉ። እርግጥ ነው
ሰው ናቸውና የስጋ ፍላጎት
ያሸንፋቸው ይሆናል። እንዲህ
ዓይነት ነገር ሲደጋገም ግን አዳዲስ
ዘዴዎችን እየቀየሱ መቆጣጠር
መልካም ነው። ቅርስ ከተሸጠ
በኋላ የዘራፊው በእስር መቀጣት
ቅርሱን እንደገና አይፈጥረውም።
ቅርስን ሊያስጠብቅ የሚችል
አሰራርና ሥነ-ምግባር መገንባት
ጥሩ ነው እላለሁ።

አንድነትን አስመልክቶ
አሁን አሁን አዲስ ፈሊጥ ይመስል
የዜጎችን ጆሮ የሚያደነቁሩ ከህግም
ከእምነትም የወጡ ነጋዴዎች
የቤተክርስቲያኗን መዝሙርና
ስብከቶች አስፓልት ላይ እያስጮኹ
ይሸጣሉ። ይህ የተጧጧፈ ንግድ
በብዙ መልኩ ፀያፍ እንደመሆኑ
ቤተክርስቲያኗ ቁርጥ ያለና የመረረ
ውሳኔ መወሰን አለባት። ያን ጊዜ
የከተማ ፖሊሶችም እንዳሁኑ ቸል
የሚሏቸው አይመስለኝም። ዳሩ
ከቤተክርስቲያን ጠንካራ ተቃውሞ
ስላልገጠማቸው የህግ ሰዎችም
አልተቃወሟቸውም።

አሁንም፡- በየቦታው
የጉዞና የጉብኝት ማስታወቂያዎች
ይሰጣሉ። እነዚህን መርሀ-ግብሮች
የሚያዘጋጇቸው ደግሞ መንፈሳዊ
የሚመስሉ የንግድ ማኀበራት
ናቸው። እነዚህን ለመቆጣጠር
ምን እየተደረገ ነው? የፈለገ
አካል በመንፈሳዊ ማኅበር ስም
በአገልጋይ ስም እየተደራጀ ህጋዊ
የሚመስል ሸማ እየለበሰ ሲኖር
የአባቶች ቁጥጥር ምን ይመስላል?
ቤተክርስቲያኗን ብሎም ህዝቡን
ችግር ላይ የሚጥል ጥገኛ ማኅበር
እንዳልሆነስ በምን ክትትል
አየተደረገ ነው?

እንግዲህ ከዚህ በላይ
የዘረዘርኳቸው በሙሉ ለአባቶች
ያነሳኋቸው ጥያቄዎች ናቸው።
ለሁሉም አዎንታዊና ተግባራዊ
ምላሽ ቢሰጥ እወዳለሁ።

የተነሳሁበትን ሐሳብ
ስደግመው፡- ቤተክርስቲያኗና
አባቶች የዚህ ህዝብ ባለአደራዎች
ናቸው። ምዕመናንና ህዝቦች
ደግሞ ለቤተክርስቲያኗ ኃላፊነት
አለባቸውና ይህንን ሁሉ ፃፍኩ።
ግና ስለመደመጤና አለመደመጤ
አሁንም እሰጋለሁ።

‹‹እየተደረበ ሁለት ሰው
ባንድ አካል

አንደበቱ ሲምል ልቦናው
ይከዳል።››

ዶ/ር ከበደ ሚካኤል
ቸር ያሰንብተን!

‹‹ሕዝባዊ ንቅናቄዎች...

ምክክር ለሥነ-ጥበብ...

ጥያቄዎች ...

Similer Documents